Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 9:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃል ላከ፤ በእስራኤልም ላይ ይወድቃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ሕዝቡ በሙሉ፤ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ጌታ የያዕቆብ ዘሮች በሆኑ በእስራኤል ሕዝብ ላይ የፍርድ ቃሉን ላከ፤ ፍርዱም ተግባራዊ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጌታ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ሞትን ላከ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ ወደቀ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጌታ በያዕቆብ ላይ ቃልን ሰደደ፥ በእስራኤልም ላይ ወደቀ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 9:8
10 交叉引用  

ለኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል ለሆነች፣ በለመለመ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት ለሆነች ጠውላጋ አበባ፣ የወይን ጠጅ ለዘራቸው መኵራሪያ ለሆነች፣ ለዚያች ከተማ ወዮላት!


ለመንግሥቱ ስፋት፣ ለሰላሙም ብዛት ፍጻሜ የለውም፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ መንግሥቱን በፍትሕና በጽድቅ ይመሠርታል፤ ደግፎ በመያዝም ያጸናዋል። በዳዊት ዙፋን ይቀመጣል፤ አገሩንም ሁሉ ይገዛል፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።


ሕዝቡ በሙሉ፣ ኤፍሬምና የሰማርያ ነዋሪዎች ይህን ያውቃሉ፤ በትዕቢትና በልብ እብሪትም እንዲህ ይላሉ፤


የሆሻያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ትዋሻለህ! አምላካችን እግዚአብሔር፣ ‘እዚያ ለመኖር ወደ ግብጽ አትሂዱ ብለህ ንገራቸው’ ብሎ አልላከህም፤


ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን ፈጽሞ አያልፍም።


跟着我们:

广告


广告