ኢሳይያስ 65:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም25 ተኵላና የበግ ጠቦት በአንድነት ይበላሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ሣር ይበላል፤ እባብ ትቢያ ይልሳል፤ በተቀደሰው ተራራዬም፣ ጕዳት አያደርሱም፤ ጥፋት አያመጡም፤” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)25 ተኩላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ ጉዳት አያደርሱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል ጌታ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም25 ተኲላና ጠቦት አብረው ይመገባሉ፤ አንበሳ እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብ ምግብ ትቢያ ይሆናል፤ እነርሱም በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም” ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)25 ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሠማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፥ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል እግዚአብሔር። 参见章节 |