Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 65:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከእንግዲህ ለሌሎች መኖሪያ ቤት አይሠሩም፤ ወይም ሌላው እንዲበላው አይተክሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ፣ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይረዝማል፤ እኔ የመረጥኋቸው፣ በእጃቸው ሥራ ለረዥም ዘመን ደስ ይላቸዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፤ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 እነርሱ የሠሩትን ቤት ሌሎች አይገቡበትም፤ የተከሉትንም ማንኛውንም ነገር ባዕዳን አይበሉትም፤ ሕዝቤ እንደ ዛፍ ለረጅም ዘመናት ይኖራሉ፤ የመረጥኳቸውም ሰዎች የደከሙበትን ነገር ለረጅም ጊዜ ይደሰቱበታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሌላ እን​ዲ​ቀ​መ​ጥ​በት አይ​ሠ​ሩም፤ ሌላም እን​ዲ​በ​ላው አይ​ተ​ክ​ሉም፤ የሕ​ዝቤ ዕድሜ እንደ ሕይ​ወት ዛፍ ዕድሜ ይሆ​ና​ልና፥ እኔም የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው በእ​ጃ​ቸው ሥራ ረዥም ዘመን ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሌላ እንዲቀመጥበት አይሠሩም፥ ሌላም እንዲበላው አይተከሉም፥ የሕዝቤ ዕድሜ እንደ ዛፍ ዕድሜ ይሆናልና፥ እኔም የመረጥኋቸው በእጃቸው ሥራ ረጅም ዘመን ደስ ይላቸዋልና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 65:22
12 交叉引用  

ማቱሳላ በአጠቃላይ 969 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።


አዳም በአጠቃላይ 930 ዓመት ከኖረ በኋላ ሞተ።


ሕይወትን ለመነህ፤ ረዥም ዘመናትንም እስከ ዘላለም ሰጠኸው።


ረዥም ዕድሜን አጠግበዋለሁ፤ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።”


እግዚአብሔር በቀኝ እጁ፣ በኀያል ክንዱም እንዲህ ሲል ምሏል፤ “ከእንግዲህ እህልሽን፣ ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤ ከእንግዲህ የደከምሽበትን፣ አዲስ የወይን ጠጅ ባዕዳን አይጠጡትም።


ነገር ግን መከሩን የሰበሰቡ ይበሉታል፤ እግዚአብሔርንም ያመሰግናሉ፤ የወይኑን ፍሬ የለቀሙም በመቅደሴ አደባባዮች ይጠጡታል።”


ስማችሁንም፣ የተመረጠው ሕዝቤ ርግማን እንዲያደርገው ትተዋላችሁ፤ ጌታ እግዚአብሔር ይገድላችኋል፤ ለአገልጋዮቹ ግን ሌላ ስም ይሰጣቸዋል።


ከያዕቆብ ዘር የሆኑትን፣ ከይሁዳም ተራሮቼን የሚወርሱትን አመጣለሁ። የተመረጠው ሕዝቤ ይወርሳቸዋል፤ ባሪያዎቼም በዚያ ይኖራሉ።


“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤


እኔም ይህን አደርግባችኋለሁ፤ ድንገተኛ ድንጋጤ፣ የሚቀሥፍ በሽታ፣ ዐይናችሁን የሚያጠፋና ሰውነታችሁን የሚያመነምን ትኵሳት አመጣባችኋለሁ፤ እህል የምትዘሩት በከንቱ ነው፤ ጠላቶቻችሁ ይበሉታልና።


跟着我们:

广告


广告