Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 63:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 “እኔ በመጭመቂያው ወይኑን ብቻዬን ረገጥሁ፤ ከመንግሥታት ማንም ከእኔ ጋራ አልነበረም፤ በቍጣዬ ረገጥኋቸው፤ በመዓቴም ጨፈለቅኋቸው፤ ደማቸው በመጐናጸፊያዬ ላይ ተረጭቷል፤ ልብሴንም በክዬዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 “መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፤ በቁጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ይመልሳል “እኔ ብቻዬን አሕዛብን ሁሉ እንደ ወይን ረገጥኩ፤ ይህን በማደርግበት ጊዜ ከሕዝቦች ከእኔ ጋር ማንም አልነበረም፤ እኔ በቊጣዬ ረገጥኳቸው፤ በመዓቴም አደቀቅኋቸው፤ ደማቸውም በልብሴ ላይ ተረጨ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 መጭ​መ​ቂ​ያ​ውን ብቻ​ዬን ረግ​ጫ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አል​ነ​በ​ረም፤ በቍ​ጣ​ዬም ረገ​ጥ​ኋ​ቸው፤ በመ​ዓ​ቴም ወደ መሬት ጣል​ጥ​ህ​ዋ​ቸው፤ ደማ​ቸ​ው​ንም በም​ድር ላይ አፈ​ሰ​ስሁ፤ ልብ​ሴም ሁሉ በደም ታለለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 መጥመቂያውን ብቻዬን ረግጫለሁ፥ ከአሕዛብም አንድ ሰው ከእኔ ጋር አልነበረም፥ በቍጣዬ ረገጥኋቸው በመዓቴም ቀጠቀጥኋቸው፥ ደማቸዋም በልብሴ ላይ ተረጭቶአል፥ ልብሴንም ሁሉ አሳድፌአለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 63:3
18 交叉引用  

አህያውን በወይን ግንድ፣ ውርንጫውንም በምርጡ የወይን ሐረግ ቅርንጫፍ ላይ ያስራል፤ ልብሱን በወይን ጠጅ፣ መጐናጸፊያውንም በወይን ጭማቂ ያጥባል።


ኢዩም፣ “ወደ ታች ወርውሯት!” አለ፤ እነርሱም ወረወሯት፤ ፈረሶቹ ሲረጋግጧትም ደሟ በግንቡና በፈረሶቹ ላይ ተረጨ።


ትዕቢተኛውን ሰው ሁሉ ተመልክተህ ዝቅ አድርገው፤ ክፉዎችንም በቆሙበት ስፍራ አድቅቃቸው።


በእግዚአብሔር ክንደ ብርቱ እንሆናለን፤ ጠላቶቻችንን የሚረጋግጥልን እርሱ ነውና።


ጌታ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በራእይ ሸለቆ፣ የመጯጯኺያ፣ የመረገጥና የሽብር፣ ቅጥሮችን የማፈራረስ፣ ወደ ተራሮችም የሚጮኽበት ቀን አለው።


የእግዚአብሔር እጅ በዚህ ተራራ ላይ ያርፋል፤ ነገር ግን ጭድ ከጭቃ ጋራ እንደሚረገጥ፣ ሞዓብም እንዲሁ ይረገጣል።


የኤፍሬም ሰካራሞች የመታበያ አክሊል፣ በእግር ይረገጣል።


ጽድቅን እንደ ጥሩር አጠለቀ፤ የድነትን ቍር በራሱ ላይ ደፋ፤ የበቀልንም ልብስ ለበሰ፤ መጐናጸፊያ እንደሚደረብም ቅናትን ደረበ።


መንግሥታትን በቍጣዬ ረጋገጥሁ፤ በመዓቴም አሰከርኋቸው፤ ደማቸውንም በምድር ላይ አፈሰስሁ።”


“በውስጤ ያሉትን ጦረኞችህ ሁሉ፣ እግዚአብሔር ተቃወመ፤ ጕልማሶቼን ለማድቀቅ፣ ሰራዊት በላዬ ላይ ጠራ፤ ድንግሊቱን የይሁዳ ሴት ልጅ፣ እግዚአብሔር በወይን መጭመቂያ ውስጥ ረገጣት።


ማጭዱን ስደዱ፤ መከሩ ደርሷልና፤ ኑ ወይኑን ርገጡ፤ የወይን መጭመቂያው ሞልቶ፣ ከጕድጓዶቹም ተርፎ ፈስሷልና፤ ክፋታቸው እንደዚህ ታላቅ ነው።”


ጠላቴም ታያለች፤ ኀፍረትንም ትከናነባለች፤ “አምላክህ እግዚአብሔር የት አለ?” ያለችኝን፣ ዐይኖቼ ውድቀቷን ያያሉ፤ አሁንም እንኳ፣ እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።


ጠላትን መንገድ ላይ እንዳለ ጭቃ ይረጋግጣሉ፤ በአንድነት እንደ ጦር ሰልፈኛ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋራ ስለ ሆነ ተዋግተው፤ ፈረሰኞችን ያዋርዳሉ።


እኔ በምሠራበት ቀን ክፉዎችን ትረግጣላችሁ፤ ከእግራችሁ ጫማ በታች ዐመድ ይሆናሉ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告