ኢሳይያስ 60:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 “ቀና በዪ፤ ዙሪያሽን ተመልከቺ፤ ሁሉም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ፣ ሴቶች ልጆችሽም በዕቅፍ ወደ አንቺ ይመጣሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሟቸዋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ቀና ብለሽ በዙሪያሽ ያለውን ሁኔታ ተመልከቺ! ሁላቸውም ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ አገር ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽም በሞግዚቶቻቸው ክንድ ሆነው ወደ አንቺ ይመጣሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ዐይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ ልጆችሽም እንደ ተሰበሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፤ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ዓይኖችሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፥ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ፥ ወንዶች ልጆችሽ ከሩቅ ይመጣሉ፥ ሴቶች ልጆችሽንም በጫንቃ ላይ ይሸከሙአቸዋል። 参见章节 |