Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 57:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ክፉዎች ግን ማዕበሉ ጭቃና ጕድፍ እንደሚያወጣ፣ ጸጥ ማለት እንደማይችል፣ እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፤ ጸጥ ሊል አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጉድፍ ያወጣሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ክፉ ሰዎች ግን እንደሚናወጥ ባሕር ናቸው፤ ውሃውም ቈሻሻውንና ጭቃውን ቀስቅሶ ያወጣል እንጂ ጸጥ አይልም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 “ኃጥ​ኣን ግን እን​ዲህ ይገ​ለ​በ​ጣሉ፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም አያ​ገ​ኙም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ክፉዎች ግን እንደሚንቀሳቀስ ባሕር ናቸው፥ ጸጥ ይል ዘንድ አይችልምና፥ ውኆቹም ጭቃና ጕድፍ ያወጣሉና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 57:20
13 交叉引用  

ይህም የሶርያን ንጉሥ እጅግ ስላበሳጨው፣ የጦር አለቆቹን ጠርቶ፣ “ከመካከላችን ከእስራኤል ንጉሥ ጋራ የተወዳጀ እንዳለ ለምን አትነግሩኝም?” ሲል ጠየቃቸው።


በደለኞች ወዮላቸው! ጥፋት ይመጣባቸዋል! የእጃቸውን ያገኛሉና።


የፊታቸው ገጽታ ይመሰክርባቸዋል፤ ኀጢአታቸውን እንደ ሰዶም በይፋ ይናገራሉ፤ አይደብቁትምም፤ ጥፋትን በራሳቸው ላይ ስላመጡ፣ ወዮላቸው!


“ለክፉዎች ሰላም የላቸውም” ይላል እግዚአብሔር።


የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በጐዳናቸውም ፍትሕ የለም፤ መንገዳቸውን ጠማማ አድርገውታል፤ በዚያም የሚሄድ ሰላም አያገኝም።


ስለ ደማስቆ፣ “ክፉ ወሬ ሰምተዋልና፣ ሐማትና አርፋድ ደንግጠዋል፤ እንደ ተናወጠ ባሕርም ታውከዋል፤ ልባቸውም ቀልጧል።


እነዚህ ሰዎች በፍቅር ግብዣችሁ ላይ ያለ አንዳች ኀፍረት ከእናንተ ጋራ ቀርበው የሚበሉ ነውረኞች ናቸው፤ ደግሞም ራሳቸውን ብቻ የሚመግቡ እረኞች ናቸው፤ እነርሱም በነፋስ የሚነዱ ዝናብ የሌላቸው ደመናዎች ናቸው፤ በመከር ወራት ፍሬ የማይገኝባቸው ከሥራቸው ተነቅለው ሁለት ጊዜ የሞቱ ዛፎች ናቸው።


የነውራቸውን ዐረፋ የሚደፍቁ የተቈጡ የባሕር ማዕበል፣ ድቅድቅ ጨለማ ለዘላለም የሚጠብቃቸው ተንከራታች ከዋክብት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告