Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 57:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የሰው መንፈስ በፊቴ እንዳይዝል፣ የፈጠርሁትም ሰው እስትንፋስ እንዳይቆም፣ ለዘላለም አልወቅሥም፤ ሁልጊዜም አልቈጣም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘለዓለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እኔ ዘወትር ሰውን አልወቅስም፤ ሁልጊዜም አልቈጣም፤ ይህን ባደርግ ኖሮ፥ የፈጠርኳቸው ሰዎች መንፈሳቸው ይዝል ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 “መን​ፈስ ከእኔ ይወ​ጣ​ልና፥ የሁ​ሉ​ንም ነፍስ ፈጥ​ሬ​አ​ለ​ሁና ለዘ​ለ​ዓ​ለም አል​ቀ​ስ​ፋ​ች​ሁም፤ ሁል​ጊ​ዜም አል​ቈ​ጣ​ች​ሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 መንፈስም የፈጠርሁትም ነፍስ ከፊቴ እንዳይዝል ለዘላለም አልጣላም፥ ሁልጊዜም አልቈጣም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 57:16
21 交叉引用  

እግዚአብሔርም፣ “ሰው ሟች ስለ ሆነ መንፈሴ እያዘነ ከርሱ ጋራ ለዘላለም አይኖርም፤ ዕድሜው 120 ዓመት ይሆናል” አለ።


የእግዚአብሔር መልአክ ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት እጁን በዘረጋ ጊዜ፣ የደረሰው ጕዳት እግዚአብሔርን ስላሳዘነው፣ ሕዝቡን የሚቀሥፈውን መልአክ “በቃ! እጅህን መልስ” አለው። የእግዚአብሔርም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


የፍጥረት ሁሉ ሕይወት፣ የሰውም ሁሉ መንፈስ በእጁ ናትና፤


የምትቈጣን ለዘላለም ነውን? ቍጣህስ ከትውልድ እስከ ትውልድ ይቀጥላልን?


ዐፈር ወደ መጣበት መሬት ሳይመለስ፣ መንፈስም ወደ ሰጠው ወደ አምላክ ሳይመለስ፣ ፈጣሪህን ዐስብ።


በጦርነትና በስደት ተፋለምሃት፤ የምሥራቅ ነፋስ እንደሚነፍስበት ቀን፣ በብርቱ ዐውሎ ነፋስ አሳደድሃት።


እግዚአብሔር ግን ምሕረት ሊያደርግላችሁ ይታገሣል፤ ርኅራኄም ሊያሳያችሁ ይነሣል። እግዚአብሔር የፍትሕ አምላክ ነውና፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁት ብፁዓን ናቸው!


ሰማያትን የፈጠረ፣ የዘረጋቸውም፣ ምድርንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ ያበጀ፣ ለሕዝቧ እስትንፋስን፣ ለሚኖሩባትም ሕይወትን የሚሰጥ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤


ይህም ሆኖ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ አባታችን ነህ፤ እኛ ሸክላዎች፣ አንተም ሸክላ ሠሪ ነህ፤ ሁላችንም የእጅህ ሥራ ነን፤


እግዚአብሔር ሆይ፤ ቅጣኝ፤ ብቻ በመጠኑ ይሁንልኝ፤ ፈጽሞ እንዳልጠፋ፣ በቍጣህ አትምጣብኝ።


ሁልጊዜ ትቈጣለህን? ቍጣህስ ለዘላለም ነውን?’ አላልሽኝም? የምትናገሪው እንዲህ ነው፤ ይሁን እንጂ የቻልሽውን ክፋት ሁሉ ታደርጊያለሽ።”


ንጉሥ ሴዴቅያስ፣ “ለኤርምያስ፣ እስትንፋስ የሰጠ ሕያው እግዚአብሔርን! በርግጥ አልገድልህም፤ ሕይወትህንም ለሚሿት አሳልፌ አልሰጥም” ብሎ በምስጢር ማለለት።


እነሆ ነፍስ ሁሉ የእኔ ናት፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች ሁሉ የልጁም ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርሷ ትሞታለች።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም፤ ርኅራኄን በመንፈግ፣ ወንድሙን በሰይፍ አሳድዶታልና፤ የቍጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣ መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤


የርስቱን ትሩፍ ኀጢአት ይቅር የሚል፣ የሚምር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማነው? ለዘላለም አትቈጣም፤ ነገር ግን ምሕረት በማድረግ ደስ ይልሃል።


ስለ እስራኤል የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው። ሰማያትን የዘረጋ፣ ምድርን የመሠረተ፣ የሰውንም መንፈስ በውስጡ የሠራ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤


ሙሴና አሮን ግን በግንባራቸው ተደፍተው፣ “የሥጋ ለባሽ ሁሉ መንፈስ አምላክ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንድ ሰው ኀጢአት በሠራ በመላው ማኅበር ላይ ትቈጣለህን?” ሲሉ ጮኹ።


ከዚህም በላይ፣ እኛ ሁላችን የሚቀጡን ምድራዊ አባቶች ነበሩን፤ እናከብራቸውም ነበር። ታዲያ ለመናፍስት አባት እንዴት አብልጠን በመገዛት በሕይወት አንኖርም!


跟着我们:

广告


广告