Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 57:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጽድቅሽንና ሥራሽን አጋልጣለሁ፤ እነርሱም አይጠቅሙሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፥ ሥራሽም አይረዳሽም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ትክክል ናቸው ብላችሁ የምታስቡአቸውን ሥራዎቻችሁን አጋልጣለሁ፤ ጣዖቶቻችሁም ሊረዱአችሁ አይችሉም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 እን​ግ​ዲህ እኔ ጽድ​ቄ​ንና የማ​ይ​ረ​ባ​ሽን የአ​ን​ቺን በደል እና​ገ​ራ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 እኔ ጽድቅሽን እናገራለሁ፥ ሥራሽም አይረባሽም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 57:12
20 交叉引用  

ሐሳባቸውን ከእግዚአብሔር ለመደበቅ፣ ወደ ጥልቅ ጕድጓድ ለሚወርዱ ሥራቸውንም በጨለማ ለሚያከናውኑ፣ “ማን ያየናል? ማንስ ያውቅብናል” ለሚሉ ወዮላቸው!


ጣዖት የሚሠሩ ሁሉ ከንቱዎች፣ የሚሠሩባቸውም ነገሮች ዋጋ ቢስ ናቸው፤ የሚናገሩላቸው ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም ያፍራሉም።


“በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር።


በደስታ ቅን ነገር የሚያደርጉትን፣ መንገድህን የሚያስቡትንም ትረዳለህ፤ እኛ ግን በእነርሱ ላይ ሳናቋርጥ ኀጢአት በመሥራታችን፣ እነሆ፤ ተቈጣህ፤ ታዲያ እንዴት መዳን እንችላለን?


የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣ በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣ በሰፈሩት ቍና ይሰፈርባቸዋል፤ ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”


“እኔም ሥራቸውንና ሐሳባቸውን ስለማውቅ፣ መንግሥታትንና ልሳናትን ሁሉ ልሰበስብ እመጣለሁ፤ እነርሱም መጥተው ክብሬንም ያያሉ።


“እናንተም፣ ‘እነዚህ ሰማያትንና ምድርን ያልፈጠሩ አማልክት ከምድር ላይ፣ ከሰማያትም በታች ይጠፋሉ’ ትሏቸዋላችሁ።”


ሁሉም ሰው ጅልና ዕውቀት የለሽ ነው። የወርቅ አንጥረኛው ሁሉ በሠራው ጣዖት ዐፍሯል፤ የቀረጻቸው ምስሎቹ የሐሰት ናቸው፤ እስትንፋስም የላቸውም።


እነርሱ ከንቱ የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፤ ፍርድ ሲመጣባቸው ይጠፋሉ።


እነርሱ ከንቱ የፌዝ ዕቃዎች ናቸው፣ ፍርድ ሲመጣባቸው ይጠፋሉ።


“እናንተ ግብዞች የኦሪት ሕግ መምህራንና ፈሪሳውያን ወዮላችሁ! ሰዎች ወደ መንግሥተ ሰማይ እንዳይገቡ በሩን ስለምትዘጉባቸው እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ መግባት የሚፈልጉትንም አታስገቡም። [


“ለመታየት ሲሉ የሚያደርጉትን ሁሉ በሰው ፊት ያደርጋሉ፤ አሸንክታባቸውን ያሰፋሉ፤ የቀሚሳቸውን ዘርፍ ያስረዝማሉ።


跟着我们:

广告


广告