Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 54:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 “አንቺ መካን፣ አንቺ ልጅ ወልደሽ የማታውቂ፣ ዘምሪ፤ እልል በዪ፤ በደስታ ጩኺ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ ባል ካላት ሴት ይልቅ፣ የፈቷ ልጆች ይበዛሉና” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፤ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ባል ካላት ሴት ይልቅ ፈት የሆነችው ልጆች ብዛት ያላቸው ስለ ሆነ፥ ልጅ እንዳልወለደችና አምጣ እንደማታውቀው ሴት የሆንሽው ኢየሩሳሌም ሆይ! እልል እያልሽ ዘምሪ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አንቺ ያልወለድሽ መካን ሆይ፥ ዘምሪ፥ አንቺ ያላማጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፥ ጩኺም፥ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆነቺቱ ልጆች በዝተዋልና፥ ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 54:1
21 交叉引用  

ሣራም፣ “እግዚአብሔር ሣቅ አድሎኛል፤ ስለዚህ፣ ይህን የሚሰማ ሁሉ ከእኔ ጋራ ይሥቃል” አለች።


መካኒቱን ሴት በቤት ያኖራታል፤ ደስተኛም የልጆች እናት ያደርጋታል። ሃሌ ሉያ።


ትንሽ እኅት አለችን፤ ጡትም ገና አላወጣችም፤ ስለ እርሷ በምንጠየቅበት ቀን ምን ማድረግ እንችል ይሆን?


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


ድምፃቸውን ከፍ ያደርጋሉ፤ በደስታም ይጮኻሉ፤ ከምዕራብም የእግዚአብሔርን ክብር ያስተጋባሉ።


ሰማያት ሆይ፤ እግዚአብሔር ይህን አድርጓልና ዘምሩ፤ የምድር ጥልቆች ሆይ፤ በደስታ ጩኹ። እናንተ ተራሮች፣ እናንተ ደኖችና ዛፎቻችሁ ሁሉ እልል በሉ፤ እግዚአብሔር ያዕቆብን ተቤዥቷል፣ በእስራኤልም ክብሩን ገልጧልና።


ሰማያት ሆይ፤ እልል በሉ፤ ምድር ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ ተራሮች ሆይ፤ በደስታ ዘምሩ! እግዚአብሔር ሕዝቡን ያጽናናል፤ ለተቸገሩትም ይራራልና።


“ፈራርሰሽ ባድማ ብትሆኚ፣ ምድርሽ ፈጽሞ ቢጠፋ፣ ዛሬ ለሕዝብሽ ጠባብ ብትሆኚም እንኳ፣ የዋጡሽ ከአንቺ ይርቃሉ።


በሐዘንሽ ዘመን የወለድሻቸው ልጆች፣ ጆሮሽ እየሰማ፣ ‘ይህ ቦታ በጣም ጠብቦናል፤ የምንኖርበት በቂ ስፍራ ስጪን’ ይሉሻል።


ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ ነገር ግን፣ “ደስታዬ በርሷ” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፣ “ባለባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባለባል ትሆናለች።


“ከማማጧ በፊት፣ ትወልዳለች፤ በምጥ ጣር ከመያዟ በፊት፣ ወንድ ልጅ ትገላገላለች።


የጽዮን ልጅ ሆይ፤ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፤ እልል በዪ፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ በፍጹም ልብሽ ደስ ይበልሽ፤ ሐሤትም አድርጊ።


አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፤ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፤ እልል በዪ፤ እነሆ፤ ጻድቁና አዳኙ ንጉሥሽ፣ ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ፣ በአህያ ግልገል፣ በውርንጫዪቱ ላይ ሆኖ ወደ አንቺ ይመጣል።


እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ “አንቺ የማትወልጅ መካን ሆይ፤ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ አምጠሽ የማታውቂ፣ በእልልታ ጩኺ፤ ባል ካላት ይልቅ፣ የብቸኛዪቱ ልጆች በዝተዋልና።”


ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤ መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።


跟着我们:

广告


广告