Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 5:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከሩብ ጋሻ የወይን ቦታ አንድ የባዶስ መስፈሪያ ያህል የወይን ጭማቂ ብቻ ይገኛል፤ አንድ የቆሮስ መስፈሪያ ዘር ተዘርቶ አንድ የኢፍ መስፈሪያ እህል ብቻ ይሰጣል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በሩብ ጋሻ መሬት ላይ የተተከለው የወይን ፍሬ ስምንት ሊትር የወይን ጭማቂ ብቻ ይወጣዋል፤ አንድ መቶ ሰማኒያ ኪሎ እህል የተዘራበትም የእርሻ ምርት ዐሥራ ስምንት ኪሎ ብቻ ይገኝበታል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዐሥር ጥማድ በሬ ካረ​ሰው የወ​ይን ቦታ አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ ይወ​ጣል፤ ስድ​ስት መስ​ፈ​ሪያ የዘራ ሦስት መሥ​ፈ​ሪያ ብቻ ያገ​ባል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከወይኑ ቦታ አሥር ጥማድ በሬ ካረሰው አንድ የባዶስ መሥፈሪያ ብቻ ይወጣል፥ አንድ የቆሮስ መሥፈሪያ ዘር አንድ የኢፍ መሥፈሪያ ብቻ ይሰጣል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 5:10
13 交叉引用  

እንቡጦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከንጹሕ ወርቅ ተሠርተው ከመቅረዙ ጋራ አንድ ወጥ ነበሩ።


ስለ ሕዝቤ ምድር፣ እሾኽና አሜከላ ስለ በቀለበት ምድር፣ ስለ ፈንጠዝያ ቤቶች ሁሉ፣ ስለዚህችም መፈንጫ ከተማ አልቅሱ።


በዚያ ቀን ሺሕ ሰቅል ብር የሚያወጣ አንድ ሺሕ የወይን ተክል የነበረበት ቦታ ሁሉ፣ ኵርንችትና እሾኽ ብቻ ይሆናል።


ከሞዓብ የአትክልት ቦታና ዕርሻ፣ ሐሤትና ደስታ ርቋል፤ የወይን ጠጅ ከመጭመቂያው እንዳይወርድ አድርቄዋለሁ፤ በእልልታ የሚጨምቀውም አይገኝም፤ በዚያ ድምፅ ቢሰማም፣ የእልልታ ድምፅ አይደለም።


ዘሩ በዐፈር ውስጥ፣ በስብሶ ቀርቷል፤ ግምጃ ቤቶቹ ፈራርሰዋል፤ ጐተራዎቹም ተሰባብረዋል፤ እህሉ ደርቋልና።


የእንጀራችሁ እህል እንዲቋረጥ በማደርግበት ጊዜ፣ ዐሥር ሴቶች በአንድ ምጣድ ላይ እንጀራ ይጋግራሉ፤ እንጀራውንም በሚዛን መዝነው እናንተም ትበላላችሁ፤ ግን አትጠግቡም።


“ ‘አንድ ሰው ከወረሰው ርስት ላይ ለእግዚአብሔር የዕርሻ መሬት ቢቀድስ፣ ዋጋው የሚተመነው ለመሬቱ በሚያስፈልገው ዘር መጠን ይሆናል፤ ይኸውም ለአንድ ሆሜር መስፈሪያ የገብስ ዘር ዐምሳ ሰቅል ጥሬ ብር ነው።


ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።”


አንድ ሰው ሃያ መስፈሪያ ወደሚሆን የእህል ክምር በመጣ ጊዜ ዐሥር ብቻ አገኘ፤ ዐምሳ ማድጋ የወይን ጠጅ ለመቅዳት ወደ መጭመቂያው በሄደ ጊዜ ሃያ ብቻ አገኘ።


በዕርሻ ላይ ብዙ ዘር ትዘራለህ፤ አንበጣ ስለሚበላው ግን፣ የምትሰበስበው ጥቂት ይሆናል።


ወይን ትተክላለህ፤ ትንከባከበዋለህ፤ ነገር ግን ትል ይበላዋልና ዘለላውን አትሰበስብም።


跟着我们:

广告


广告