ኢሳይያስ 49:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በተወደደ ጊዜ እመልስልሃለሁ፤ በድነት ቀን እረዳሃለሁ። ለሕዝቡ ቃል ኪዳን እንድትሆን፣ ምድሪቱን እንደ ገና እንድትሠራት፣ ጠፍ የሆኑትን ርስቶች ለየባለቤታቸው እንድትመልስ፣ እጠብቅሃለሁ፤ እሠራሃለሁም፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመዳንም ቀን ረድቼሃለሁ፤ እጠብቅሃለሁ፥ ምድርንም እንድታቀና፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች እንድታወርስ፥ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በመረጥኩት ሰዓት ለጸሎትህ መልስ እሰጥሃለሁ፤ በመዳንም ቀን እረዳሃለሁ፤ ምድሪቱን መልሰህ እንድታቋቋምና ውድማ የሆነውን መሬት እንድታከፋፍል ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በተመረጠችው ዕለት ሰምቼሃለሁ፤ ድኅነት በሚደረግበትም ቀን ረድቼሃለሁ፤ ቃል ኪዳን አድርጌ ለሕዝቡ ሰጥቼሃለሁ፤ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትን ርስቶች ትወርስ ዘንድ፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በተወደደ ጊዜ ሰምቼሃለሁ፥ በመድኃኒትም ቀን ረድቼሃለሁ፥ እጠብቅህማለሁ፥ ምድርንም ታቀና ዘንድ፥ ውድማ የሆኑትንም ርስቶች ታወርስ ዘንድ፥ 参见章节 |