Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 43:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በባሕር ውስጥ መንገድ፣ በማዕበል ውስጥ መተላለፊያ ያበጀ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታ እንዲህ ይላል፥ በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እግዚአብሔር በባሕር መካከል መንገድን ሠራ፤ በውሃ መካከል መተላለፊያን አበጀ፥

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በባ​ሕር ውስጥ መን​ገ​ድን በኀ​ይ​ለ​ኛም ውኃ ውስጥ መተ​ላ​ለ​ፊ​ያን ያደ​ረገ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ እን​ዲህ ይላል፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እግዚአብሔር በባሕር ውስጥ መንገድን በኃይለኛም ውኃ ውስጥ መተላለፊያን ያደርጋል፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 43:16
21 交叉引用  

በደረቅ ምድር እንዲሻገሩ ባሕሩን በፊታቸው ከፈልህ፤ ያሳደዷቸውን ግን በኀይለኛ ውሃ ውስጥ እንደሚጣል ድንጋይ ወደ ጥልቁ ውስጥ ወረወርሃቸው።


ቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ፤ በምድረ በዳ እንደሚታለፍ በጥልቅ ውሃ መካከል መራቸው።


መንገድህ በባሕር ውስጥ ነው፤ መሄጃህም በታላቅ ውሃ ውስጥ ነው፤ ዱካህ ግን አልታወቀም።


በሙሴና በአሮን እጅ፣ ሕዝብህን እንደ በግ መንጋ መራኸው።


ባሕሩን ከፍሎ አሻገራቸው፤ ውሃውንም እንደ ክምር አቆመ።


ውሃውን ለመክፈል በትርህን አንሣና እጅህን በባሕሩ ላይ ዘርጋ፤ እስራኤላውያን በባሕሩ ውስጥ በየብስ ይሻገራሉ።


እስራኤላውያን ግን ውሃው ግራና ቀኝ እንደ ግድግዳ ሆኖ፣ በደረቅ ምድር ባሕሩን ተሻገሩ።


በውሃ ውስጥ በምታልፍበት ጊዜ፣ ከአንተ ጋራ እሆናለሁ፤ ወንዙን ስትሻገረው፣ አያሰጥምህም፤ በእሳት ውስጥ ስትሄድ፣ አያቃጥልህም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።


ጥልቁን ውሃ፣ ‘ደረቅ ሁን፤ ወንዞችህን አደርቃለሁ’ እላለሁ።


በመጣሁ ጊዜ ለምን በዚያ ሰው አልነበረም? በተጣራሁስ ጊዜ የሚመልስ ሰው እንዴት በዚያ ታጣ? ስለ እናንተ ወጆ ለመክፈል ክንዴ ዐጥራ ነበርን? እናንተንስ ለማዳን ኀይል አነሰኝን? እነሆ፤ በተግሣጼ ባሕሩን አደርቃለሁ፤ ወንዞችን ምድረ በዳ አደርጋለሁ፤ ዓሦቻቸው ውሃ በማጣት ይሸታሉ፤ በጥማትም ይሞታሉ።


የዳኑት እንዲሻገሩ ባሕሩን፣ የታላቁን ጥልቅ ውሆች ያደረቅህ፣ በጥልቁም ውስጥ መንገድ ያበጀህ፣ አንተ አይደለህምን?


ሞገዱ እንዲተምም ባሕሩን የማናውጥ፣ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና፤ ስሙም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


በቀን እንድታበራ፣ ፀሓይን የመደበ፣ በሌሊት እንዲያበሩ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን ያዘዛቸው፣ የሞገዱ ድምፅ እንዲተምም፣ ባሕሩን የሚያናውጥ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነ እንዲህ ይላል፤


ስድስተኛውም መልአክ ጽዋውን በታላቁ ወንዝ በኤፍራጥስ ላይ አፈሰሰ፤ ከምሥራቅ ለሚመጡ ነገሥታት መንገድ እንዲዘጋጅላቸው የወንዙ ውሃ ደረቀ።


跟着我们:

广告


广告