Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 43:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የእስራኤል ቅዱስ፣ የሚቤዣችሁ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ ሰራዊት እሰድዳለሁ፤ በሚመኩባቸውም መርከቦች፣ ባቢሎናውያንን ሁሉ እንደ ኰብላይ አመጣለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አዳኛችሁ የእስራኤል ቅዱስ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ስለ እናንተ በባቢሎን ላይ የሚዘምት ሠራዊት እልካለሁ፤ የከተማዋን ቅጽር በሮች እሰባብራለሁ፤ የባቢሎናውያንም ፉከራ ወደ ለቅሶ ይለወጣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ የሚ​ቤ​ዣ​ችሁ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ስለ እና​ንተ ወደ ባቢ​ሎን ሰድ​ጃ​ለሁ፤ ስደ​ተ​ኞ​ችን አስ​ነ​ሣ​ለሁ፤ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም በመ​ር​ከብ ውስጥ ይታ​ሰ​ራሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የእስራኤል ቅዱስ፥ የሚቤዣችሁ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ እናንተ ወደ ባቢሎን ሰድጃለሁ፥ ከላዳውያንንም ሁሉ ስደተኞች አድርጌ በሚመኩባቸው መርከቦች አዋርዳቸዋለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 43:14
23 交叉引用  

የሚቤዠኝ ሕያው እንደ ሆነ፣ በመጨረሻም በምድር ላይ እንደሚቆም ዐውቃለሁ።


ዐለቴና አዳኜ እግዚአብሔር ሆይ፤ የአፌ ቃልና የልቤ ሐሳብ፣ በፊትህ ያማረ ይሁን።


እነሆ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ተመልከቱ፤ ሕዝቡ ከንቱ ሆኗል! አሦራውያን የምድረ በዳ አራዊት መፈንጪያ አደረጓት፤ የግንብ ማማቸውን ሠሩባት፤ ምሽጎቿን አወደሙ፤ የፍርስራሽ ክምር አደረጓት።


አንተ ትል ያዕቆብ፣ ታናሽ እስራኤል ሆይ፤ ‘አትፍራ እኔ እረዳሃለሁ’ ” ይላል እግዚአብሔር፤ የሚቤዥህ የእስራኤል ቅዱስ ነው።


አሁን ግን፣ ያዕቆብ ሆይ የፈጠረህ፣ እስራኤል ሆይ! የሠራህ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህ ጠርቼሃለሁ፤ አንተ የእኔ ነህ፤


“ከማሕፀን የሠራህ፣ የተቤዠህም፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ሁሉን ነገር የፈጠርሁ፣ ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ ምድርን ያንጣለልሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


“የእስራኤል ንጉሥና ቤዛ እግዚአብሔር፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ የፊተኛውም እኔ ነኝ፤ የኋለኛውም እኔ ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም።


የሚቤዠን የእስራኤል ቅዱስ፣ ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ነው።


የተቤዠህ፣ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ፣ የሚበጅህ ምን እንደ ሆነ የማስተምርህ፣ መሄድ በሚገባህ መንገድ የምመራህ ነኝ።


አንቺ በብዙ ውሃ አጠገብ የምትኖሪ፣ በሀብትም የበለጸግሽ ሆይ፤ የምትወገጂበት ጊዜ ወጥቷል፤ ፍጻሜሽ ደርሷል።


“በጽዮን ላይ ስላደረሱት ጥፋት ሁሉ ለባቢሎንና በባቢሎን ለሚኖሩት ሁሉ ዐይናችሁ እያየ ዋጋቸውን እከፍላቸዋለሁ” ይላል እግዚአብሔር።


“ ‘ቅዱሱ ስሜ በሕዝቤ በእስራኤል ዘንድ እንዲታወቅ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ቅዱስ ስሜ እንዲናቅ፣ እንዲቃለል አልፈልግም፤ አሕዛብም እኔ እግዚአብሔር የእስራኤል ቅዱስ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።


የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ተጨነቂ፤ አሁንስ ከከተማ ወጥተሽ፣ በሜዳ ላይ መስፈር አለብሽና፤ ወደ ባቢሎን ትሄጃለሽ፤ በዚያ ከጠላት እጅ ትድኛለሽ። እግዚአብሔር በዚያ፣ ከጠላቶችሽ ይታደግሻል።


እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፤ “መጽሐፉን ልትወስድ፣ ማኅተሞቹንም ልትፈታ ይገባሃል፤ ምክንያቱም ታርደሃል፤ በደምህም ከነገድ ሁሉ፣ ከቋንቋ ሁሉ፣ ከወገን ሁሉ፣ ከሕዝብ ሁሉ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ዋጅተሃል።


跟着我们:

广告


广告