Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 41:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ጠላቶችህን ብትፈልጋቸው እንኳ፣ አታገኛቸውም፤ የሚዋጉህም፣ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የሚጣሉህንም ትፈልጋቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ጠላቶችህን ትፈልጋቸዋለህ፤ ነገር ግን አታገኛቸውም፤ በአንተ ላይ ጦርነት አስነሥተው የነበሩትም ፈጽሞ እንዳልነበሩ ይሆናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​ህ​ንም ሰዎች ትሻ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አታ​ገ​ኛ​ቸ​ው​ምም፤ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ይሆ​ና​ሉና፤ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሚያጣሉህንም ትሻቸዋለህ አታገኛቸውምም፥ የሚዋጉህም እንዳልነበሩና እንደ ምናምን ይሆናሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 41:12
7 交叉引用  

እነሆ፤ ሲመሽ ድንገተኛ ሽብር ሆነ! ከመንጋቱ በፊት ግን አንዳቸውም አልተገኙም። የዘረፉን ዕድል ፈንታ፣ የበዘበዙን ዕጣ ይህ ሆነ።


የተራበ ሰው በሕልሙ ሲበላ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ ራቡ እንዳልለቀቀው፣ የጠማውም ሰው በሕልሙ ሲጠጣ ዐድሮ፣ ነገር ግን ሲነቃ እንደ ዛለና ጥማቱም እንዳልተወው፣ የጽዮንን ተራራ የሚወጋ፣ የአሕዛብ መንጋ ሁሉ እንዲሁ ይሆናል።


መኳንንቷም መንግሥት ተብለው ለመጠራት የሚያስችላቸው ነገር አይኖራቸውም፤ አለቆቿም በሙሉ ጥርግ ብለው ይጠፋሉ።


እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “ከተዋጊዎች ላይ ምርኮኞች በርግጥ ይወሰዳሉ፤ ከጨካኞችም ላይ ምርኮ ይበዘበዛል፤ ከአንቺ ጋራ የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፤ ልጆችሽንም እታደጋለሁ።


በዚያ ጊዜ፣ ያስጨነቁሽን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዐንካሶችን እታደጋለሁ፤ የተበተኑትንም እሰበስባለሁ፤ በተዋረዱበት ምድር ሁሉ፣ ለውዳሴና ለክብር አደርጋቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告