Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 40:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ድምፅም፣ “ጩኽ” አለኝ፤ እኔም፣ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 አንድ ድምጽ “ጩኽ!” አለኝ፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልኩ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አንድ ድምፅ “የዐዋጅ ቃል ተናገር!” እያለ ይጮኻል። እኔም “ምን ብዬ ላውጅ!” ስል ጠየቅሁ። ያም ድምፅ “እንዲህ ብለህ ዐውጅ” አለኝ፦ “ሰው ሁሉ እንደ ሣር ነው፤ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰ​ውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ጩኽ የሚል ሰው ቃል፥ ምን ብዬ ልጩኽ? አልሁ። ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ምድረ በዳ አበባ ነው።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 40:6
17 交叉引用  

እንደ አበባ ይፈካል፤ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላ ይፈጥናል፤ አይጸናምም።


ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።


ክፉዎች እንደ ሣር ቢበቅሉ፣ ክፉ አድራጊዎች ቢለመልሙ፣ ለዘላለሙ ይጠፋሉ።


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


የሕዝቦቻቸው ኀይል ተሟጥጧል፤ ደንግጠዋል፤ ተዋርደዋልም፤ በሜዳ እንዳሉ ዕፀዋት፣ እንደ ለጋ ቡቃያ፣ በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፣ በእንጭጩ ዋግ እንደ መታው ሆነዋል።


የዐዋጅ ነጋሪ ድምፅ እንዲህ ይላል፤ “በምድረ በዳ የጌታን መንገድ፣ አዘጋጁ፤ ለአምላካችን አውራ ጐዳና፣ በበረሓ አስተካክሉ።


“የማጽናናችሁ እኔ፣ እኔው ብቻ ነኝ፤ ሟች የሆኑትን ሰዎች፣ እንደ ሣር የሚጠወልጉትን የሰው ልጆች ለምን ትፈራለህ?


“በኀይል ጩኽ፤ ምንም አታስቀር፤ ድምፅህን እንደ መለከት አሰማ፤ ለሕዝቤ ዐመፃቸውን፣ ለያዕቆብም ቤት ኀጢአታቸውን ተናገር።


“ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ ‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣ በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣ በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣ እንዴት እንደ ተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።


ጠባቂዎች፣ በኤፍሬም ኰረብቶች ላይ፣ ‘ኑ፤ ወደ ጽዮን፣ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር እንውጣ!’ ብለው የሚጮኹበት ቀን ይመጣል።”


“በጊብዓ መለከትን፣ በራማ እንቢልታን ንፉ፤ በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤ ‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።


ከዚያም ከእኔ ጋራ ይነጋገር የነበረው መልአክ እንዲህ አለኝ፤ “ይህን ቃል ተናገር፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ስለ ጽዮንና ስለ ኢየሩሳሌም እጅግ ቀንቻለሁ፤


跟着我们:

广告


广告