Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 36:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን ከብዙ ሰራዊት ጋራ ከለኪሶ፣ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወዳለበት፣ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። የጦር አዛዡም ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ፣ በላይኛው ኵሬ ቦይ አጠገብ ደርሶ ቆመ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከዚያ የአሦር ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው። እርሱም በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ላይ ባለችው በላይኛይቱ ኩሬ መስኖ አጠገብ በቆመ ጊዜ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ንጉሥ ሕዝቅያስ እጁን እንዲሰጥ ይጠይቀው ዘንድ የአሦር ንጉሥ የጦር አዛዡን፥ ከብዙ ሠራዊት ጋር ከላኪሽ ወደ ኢየሩሳሌም ላከው፤ እርሱም ሄዶ የላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አካባቢ በሚገኘው በልብስ አጣቢው ቦታ አጠገብ ቆመ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የአ​ሦ​ርም ንጉሥ ራፋ​ስ​ቂ​ስን ከብዙ ሠራ​ዊት ጋር ከለ​ኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ላከው፤ እር​ሱም በአ​ጣ​ቢው እርሻ መን​ገድ ባለ​ችው በላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኵሬ መስኖ አጠ​ገብ ቆመ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 የአሦርም ንጉሥ ራፋስቂስን ከብዙ ሠራዊት ጋር ከለኪሶ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝቅያስ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፥ እርሱም በአጣቢው እርሻ መንገድ ባለችው በላይኛይቱ ኵሬ መስኖ አጠገብ ቆመ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 36:2
10 交叉引用  

ወደ ከተማዪቱም መልእክተኞች በመላክ የእስራኤልን ንጉሥ አክዓብን እንዲህ አለው፤ “ቤን ሃዳድ እንዲህ ይላል፤


የአሦር ንጉሥ እስራኤልን ማርኮ ወደ አሦር በማፍለስ በአላሔ፣ በጎዛን ውስጥ በአቦር ወንዝ አጠገብና በማዴ ከተሞች አሰፈራቸው።


“ ‘አሁን ናና፣ ከጌታዬ ከአሦር ንጉሥ ጋራ ተደራደር፤ የሚጋልቧቸው ሰዎች ካሉህ፣ ሁለት ሺሕ ፈረሶች እሰጥሃለሁ!


እግዚአብሔርም ኢሳይያስን እንዲህ አለው፤ “አንተና ልጅህ ሸአር ያሹብ አካዝን ለመገናኘት ወደ ልብስ ዐጣቢው ዕርሻ በሚወስደው መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው የኵሬ መስኖ ጫፍ ውጡ፤


በዚህም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ኢየሩሳሌምንና የቀሩትን የይሁዳ ከተሞች ለኪሶንና ዓዜቃን እየወጋ ነበር፤ ከተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችም የቀሩት እነዚሁ ብቻ ነበሩና።


እናንተ በለኪሶ የምትኖሩ፣ ፈረሶችን ከሠረገላው ጋራ አያይዙ፤ ለጽዮን ሴት ልጅ፣ የኀጢአት መጀመሪያ እናንተ ነበራችሁ፤ የእስራኤል በደል በእናንተ ዘንድ ተገኝቷልና።


ቍስሏ የማይሽር ነውና፤ ለይሁዳ ተርፏል፤ እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣ እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሷል።


跟着我们:

广告


广告