Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 34:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 የኤዶም ምንጮች ሬንጅ፣ ዐፈሯ የሚቃጠል ድኝ፣ ምድሯም የሚንበለበል ዝፍት ይሆናል!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 የኤዶሚያስም ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፥ አፈርዋም ዲን ይሆናል፥ መሬትዋም የሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የኤዶም ጅረቶች ወደ ቅጥራንነት፥ ዐፈሩም ወደ ዲንነት ይለወጣሉ፤ ከዚያም ሀገሪቱ በመላ ትቃጠላለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ሸለ​ቆ​ዎ​ችዋ ዝፍት ሆነው ይወ​ጣሉ፤ አፈ​ር​ዋም ዲን ይሆ​ናል፤ መሬ​ቷም በቀ​ንና በሌ​ሊት እንደ ዝፍት ይቃ​ጠ​ላል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም አይ​ጠ​ፋም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 የኤዶሚያስም ፈሳሾች ዝፍት ሆነው ይለወጣሉ፥ አፈርዋም ዲን ይሆናል፥ መሬትዋም የሚቃጠል ዝፍት ትሆናለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 34:9
10 交叉引用  

ሰዶምንና ገሞራን፣ እንዲሁም በረባዳው ስፍራ የሚገኘውን ምድር ሁሉ ቍልቍል ተመለከተ፤ ከእቶን የሚወጣ የመሰለ ጥቅጥቅ ያለ ጢስ ከምድሪቱ ወደ ላይ ሲትጐለጐል አየ።


ድንኳኑ በእሳት ይያያዛል፤ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።


እርሱ በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምና ዲን ያዘንባል፤ የጽዋቸውም ዕጣ ፈንታ፣ የሚለበልብ ዐውሎ ነፋስ ነው።


ከቀድሞ ጀምሮ ቶፌት የተባለ የማቃጠያ ስፍራ ተዘጋጅቷል፤ ለንጉሡም ተበጅቷል፤ ማንደጃ ጕድጓዱም ሰፊና ጥልቅ ነው፤ በውስጡም ብዙ እሳትና ማገዶ አለ፤ የእግዚአብሔርም እስትንፋስ እንደ ፈሳሽ ድኝ ያቀጣጥለዋል።


ባሶራ ፈራርሳ የድንጋጤ፣ የመዘባበቻና የርግማን ምልክት እንደምትሆን በራሴ ምያለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከተሞቿም ሁሉ ለዘላለም ባድማ ይሆናሉ።”


ሎጥ ከሰዶም በወጣበት ዕለት ግን እሳትና ዲን ከሰማይ ዘንቦ በሙሉ አጠፋቸው።


ምድሪቱ በሙሉ የተቃጠለ ጨውና ዲን ዐመድ ትሆናለች። አንዳች ነገር አይተከልባትም፤ ምንም ነገር አያቈጠቍጥባትም፤ የሚያድግ ተክል አይገኝባትም። የሚደርስባት ውድመት እግዚአብሔር በታላቅ ቍጣ እንደ ገለባበጣቸው እንደ ሰዶምና ገሞራ፣ እንደ አዳማና ስቦይ ጥፋት ይሆናል።


እንዲሁም ሰዶምና ገሞራ፣ በዙሪያቸውም ያሉ ከተሞች ለሴሰኛነትና ከተፈጥሮ ሥርዐት ውጭ ለሆነ ሩካቤ ሥጋ ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፤ እነርሱም በዘላለም እሳት በመቀጣት ለሚሠቃዩት ምሳሌ ሆነዋል።


ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።


ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”


跟着我们:

广告


广告