ኢሳይያስ 34:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ጕጕት በዚያ ጐጆ ሠርታ ዕንቍላል ትጥላለች፤ ትቀፈቅፋለች፤ ጫጩቶቿን በክንፎቿ ትታቀፋቸዋለች፤ ጭላቶችም ጥንድ ጥንድ ሆነው፣ ለርቢ በዚያ ይሰበሰባሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 በዚያም ጉጉት ጎጆ ሠርታ እንቁላልን ትጥላለች፥ ትቀፈቅፋለችም፤ ጫጩቶቿንም በክንፏ ትሰበስባለች፤ በዚያም ደግሞ አሞራዎች ጥንድ ጥንድ ሆነው ይሰበሰባሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 በዚያም ጒጒቶች ጎጆ ሠርተው እንቊላል ይጥላሉ፤ እንቁላሎቻቸውንም ፈልፍለው በክንፎቻቸው ጥላ ሥር ይንከባከባሉ፤ አሞራዎችም ከጓደኞቻቸው ጋር በዚያ ይሰባሰባሉ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 በዚያ ጃርቶች ይዋለዳሉ፤ ምድርም ልጆችዋን በኀይል ታድናለች፤ ዋሊያዎች በዚያ ይገናኛሉ፤ ፊት ለፊትም ይተያያሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 በዚያም ዋሊያ ቤትዋን ትሠራለች እንቍላልን ትጥላለች ትቀፈቅፈውማለች ልጆችዋንም በጥላዋ ትሰበስባለች፥ በዚያም ደግሞ አሞራዎች እያንዳንዳቸው ከባልንጀሮቻቸው ጋር ይሰበሰባሉ። 参见章节 |