Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 33:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር በዚያ ኀይላችን ይሆናል፤ ባለመቅዘፊያ ጀልባዎች እንደማያልፉባቸው፣ ታላላቅ መርከቦችም እንደማይሻገሯቸው፣ ሰፋፊ ወንዞችና ጅረቶች ይሆንልናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እዚያም ማንም ጀልባዎችን በማይቀዝፍባቸውና ትላልቅ መርከቦች በማይንሳፈፉባቸው በወንዞችና በሰፋፊ ጅረቶች እግዚአብሔር በታላቅ ግርማው ከእኛ ጋር ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለእ​ና​ንተ ታላቅ ነው፤ ሀገ​ራ​ች​ሁም የሰፉ ወን​ዞ​ችና ታላቅ የመ​ስኖ ስፍራ ይሆ​ናል፤ በዚ​ህች መን​ገድ አት​ሄ​ድም፤ መር​ከ​ቦ​ችም አይ​ሄ​ዱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እግዚአብሔር በዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ ከእኛ ጋር በግርማ ይሆናል፥ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፥ ታላላቆችም መርከቦች አያልፉባትም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 33:21
14 交叉引用  

የእግዚአብሔር ድምፅ በውሆች ላይ ነው፤ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፤ እግዚአብሔር በታላላቅ ውሆች ላይ አንጐደጐደ።


የጽዮን ሕዝብ ሆይ፤ እልል በሉ፤ በደስታም ዘምሩ፤ በመካከላችሁ ያለው የእስራኤል ቅዱስ ታላቅ ነውና።”


ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ በሩቅ የተዘረጋችውንም ምድር ይመለከታሉ።


በተራቈቱ ኰረብቶች ላይ ወንዞችን፣ በሸለቆዎች ውስጥ ምንጮችን አፈልቃለሁ። ምድረ በዳውን የውሃ ኵሬ፣ የተጠማውን ምድር የውሃ ምንጭ አደርጋለሁ።


እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤


የምድረ በዳ አራዊት፣ ቀበሮና ጕጕት ያከብሩኛል፤ በምድረ በዳ ውሃ፣ በበረሓም ምንጭ እሰጣለሁና። ለመረጥሁት ሕዝቤ ውሃ እሰጣለሁ፤


ትእዛዜን ሰምተህ ብቻ ቢሆን ኖሮ፣ ሰላምህ እንደ ወንዝ፣ ጽድቅህም እንደ ባሕር ሞገድ በሆነ ነበር።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ሰላምን እንደ ወንዝ ውሃ አፈስስላታለሁ፤ የመንግሥታትንም ብልጽግና እንደ ጅረት ውሃ አጐርፍላታለሁ፤ ትጠባላችሁ፤ በዕቅፏም ትያዛላችሁ፤ በጭኖቿም ላይ ትፈነድቃላችሁ።


እነሆ፤ እጄን በእነርሱ ላይ አነሣለሁ፤ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል፤ ከዚያም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔን እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።


“በያዕቆብ መጥፎ ነገር አልተገኘም፤ በእስራኤልም ጕስቍልና አልታየም፤ እግዚአብሔር አምላኩ ከርሱ ጋራ ነው፤ የንጉሡም እልልታ በመካከላቸው ነው።


እስጢፋኖስም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ወንድሞችና አባቶች ሆይ፤ አድምጡኝ! አባታችን አብርሃም ወደ ካራን ከመምጣቱ በፊት፣ ገና በመስጴጦምያ ሳለ፣ የክብር አምላክ ተገልጦለት፣


አንድ ባሪያ ከአሳዳሪው ኰብልሎ ወደ አንተ ቢመጣ፣ ለአሳዳሪው አሳልፈህ አትስጠው።


跟着我们:

广告


广告