Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 33:19 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እነዚያ ንግግራቸው የማይገባ፣ የሚሉትም የማይታወቅ፣ ሊረዱት የማይቻል ቋንቋ የሚናገሩትን ጋጠወጥ ሕዝብ ከእንግዲህ አታያቸውም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከእንግዲህ ወዲህ ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል የማይገባ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ አታይም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እናንተ ልታስተውሉትና ልትረዱት በማትችሉት ቋንቋ የሚንተባተቡባችሁን እብሪተኞች ባዕዳን ሕዝቦችን ከእንግዲህ ወዲህ አታዩአቸውም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የማ​ታ​ው​ቋ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እና​ንት ዐማ​ፅ​ያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገ​ርን ትሰ​ማ​ላ​ችሁ። የሚ​ሰ​ማም ማስ​ተ​ዋል እን​ደ​ሌ​ለው ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጨካኝን ሕዝብ፥ ቋንቋው ለማስተዋል ጥልቅ የሆነውንና አንደበቱ ለማስተዋል ጸያፍ የሆነውን ሕዝብ፥ አታይም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 33:19
10 交叉引用  

ኑ እንውረድ፤ እርስ በርሳቸውም እንዳይግባቡ ቋንቋቸውን እንደበላልቀው።”


“ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ አሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ “ ‘ወደዚህች ከተማ ፈጽሞ አይገባም፤ ፍላጻም አይወረውርባትም፤ ጋሻ አንግቦ አይቀርብም፤ በዐፈርም ቍልል አይከብባትም።


ሙሴም ለሕዝቡ መለሰላቸው፤ “አትሸበሩ፣ ጸንታችሁ ቁሙ፤ እግዚአብሔር ዛሬ የሚያደርግላችሁን መታደግ ታያላችሁ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብጻውያንን ዳግም አታዩአቸውም።


እንግዲያው እግዚአብሔር፣ በባዕድ ልሳን በእንግዳ ቋንቋ ለዚህ ሕዝብ ይናገራል።


በመጣበት መንገድ ይመለሳል፤ ወደዚህች ከተማም አይገባም” ይላል እግዚአብሔር።


ስለዚህ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ወደ ነነዌም ተመልሶ በዚያ ተቀመጠ።


የእስራኤል ቤት ሆይ፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከሩቅ ሕዝብን አመጣባችኋለሁ፤ ጥንታዊና ብርቱ፣ ቋንቋውን የማታውቁት፣ ንግግሩንም የማትረዱት ሕዝብ ነው።


በሕግም እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፣ በባዕዳንም አንደበት፣ ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፤” ይላል ጌታ።


跟着我们:

广告


广告