Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 30:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ስለዚህ ይህ ኀጢአት፣ ተሰነጣጥቆ ሊወድቅ እንደ ደረሰ፣ ሳይታሰብ ድንገት እንደሚወድቅ ረዥም ቅጥር ይሆንባችኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ ይህ በደላችሁ ተሰነጣጥቆ በማኰፍኰፍ ሊወድቅ እንደ ተቃረበና አወዳደቁም በፍጥነትና በቅጽበት እንደሚደርስበት እንደ ረጅም የቅጽር ግንብ ያደርጋችኋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ስለ​ዚህ ይህ በደል አዘ​ብ​ዝቦ ለመ​ፍ​ረስ እንደ ቀረበ፥ አፈ​ራ​ረ​ሱም ፈጥኖ ድን​ገት እን​ደ​ሚ​መጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆ​ን​ባ​ች​ኋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ረጅም ቅጥር ይሆንባችኋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 30:13
19 交叉引用  

የቀሩት ወደ አፌቅ ከተማ ሸሹ፤ በዚያም በሃያ ሰባቱ ሺሕ ላይ ቅጥሩ ተንዶ ወደቀባቸው። ቤን ሃዳድም ወደ ከተማዪቱ ሸሽቶ በመሄድ ወደ አንዲት እልፍኝ ገብቶ ተደበቀ።


ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣ የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።


ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው? ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣ ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?


ከታላቅ ክብሩ ሊያዋርዱት፣ ይህን አንድ ነገር ወጠኑ፤ ሐሰት ባለበት ነገር ደስ ይሰኛሉ፤ በአፋቸው ይመርቃሉ፤ በልባቸው ግን ይራገማሉ። ሴላ


ከብዙ ተግሣጽ በኋላ ዐንገቱን የሚያደነድን ሰው፣ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።


ስለዚህ በቅጽበት መዓት ይወርድበታል፤ በድንገት ይጠፋል፤ መዳኛም የለውም።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን ገለጠልኝ፤ እንዲህም ሲል በጆሮዬ ሰማሁ፤ “ይህ ኀጢአት እስከምትሞቱበት ቀን ድረስ አይሰረይላችሁም” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣ እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤ የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም።


ነገር ግን ብዙ ጠላቶችሽ እንደ ትቢያ ብናኝ፣ የጨካኞች መንጋ በነፋስ እንደሚነዳ ገለባ ይሆናሉ። ድንገት ሳይታሰብም፣


እግዚአብሔር የሕዝቡን ስብራት ሲጠግን፣ ያቈሰለውንም ሲፈውስ፣ ጨረቃ እንደ ፀሓይ ታበራለች፤ የፀሓይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት ዕጥፍ ይደምቃል።


ጥፋት ይመጣብሻል፤ ነገር ግን በአስማትሽ እንዴት እንደምታርቂው አታውቂም፤ ወጆ ከፍለሽ ለማስወገድ የማትችዪው፣ ጕዳት ይወድቅብሻል፤ ያላሰብሽው አደጋ፣ ድንገት ይደርስብሻል።


የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤ እኔም ድንገት ሠራሁ፤ እነርሱም ተፈጸሙ።


ወገኖችህ የቀድሞ ፍርስራሾችን መልሰው ይሠራሉ፤ የጥንቱንም መሠረት ያቆማሉ፤ አንተም፣ የተናዱ ቅጥሮችን ዐዳሽ፣ ባለአውራ መንገድ ከተሞችን ጠጋኝ ትባላለህ።


የእናንተን ኀጢአት የአባቶቻችሁንም ኀጢአት እበቀላለሁ” ይላል እግዚአብሔር። “በተራሮች ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ስላቀረቡ፣ በኰረብቶች ላይ ስለ ሰደቡኝ፣ በሰፈሩት ቍና ይሰፈርባቸዋል፤ ስለ ቀደሙት ሥራዎቻቸውም የእጃቸውን ያገኛሉ።”


ዶፍ ወረደ፤ ጐርፍም ጐረፈ፤ ነፋስም ነፈሰ፤ ያን ቤት መታው፤ ቤቱም ወደቀ፤ አወዳደቁም የከፋ ነበር።”


ቃሌን ሰምቶ የማይፈጽም ግን ቤቱን ያለ መሠረት በዐፈር ላይ የሠራን ሰው ይመስላል፤ የወንዝ ሙላትም ቤቱን በመታው ጊዜ ወዲያው ወደቀ፤ ክፉኛም ፈራረሰ።”


跟着我们:

广告


广告