ኢሳይያስ 28:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም22 እንግዲህ ፌዛችሁን አቁሙ፤ አለዚያ እስራታችሁ ይጸናባችኋል፤ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ መላውን ምድር ለማጥፋት ያወጀውን ዐዋጅ ሰምቻለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ጌታ የሠራዊት አምላክ አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት መወሰኑን ስለ ሰማሁ ማፌዝ ይቅርባችሁ፤ አለበለዚያ እስራታችሁ ይጠብቅባችኋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚያደርገውን ያለቀና የተቈረጠ ነገርን ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራታችሁ እንዳይጸናባችሁ እናንተ ደስ አይበላችሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራት እንዳይጸናባችሁ አታፊዙ። 参见章节 |