Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 26:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር ሆይ፤ የፀነሰች ሴት ልትወልድ ስትል፣ በምጥ እንደምትጨነቅና እንደምትጮኽ፣ እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ ጌታ፥ በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 አምላክ ሆይ! ምጥ የያዛት ሴት በሕመሙ ተጨንቃ እንደምትጮኽ፥ እኛም በፊትህ እንዲሁ ሆነናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የፀ​ነ​ሰች ሴት ለመ​ው​ለድ ስት​ቀ​ርብ እን​ደ​ም​ት​ጨ​ነ​ቅና በምጥ እን​ደ​ም​ት​ጮህ፥ አቤቱ፥ እን​ዲሁ በፊ​ትህ ለወ​ዳ​ጅህ ሆነ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የፀነሰች ሴት ለመውለድ ስትቀርብ እንደምትጨነቅና በምጥ አንደምትጮኽ፥ አቤቱ፥ እንዲሁ በፊትህ ሆነናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 26:17
11 交叉引用  

ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”


ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ በዚያ ብርክ ያዛቸው።


ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።


ወገቤ በዚህ ሥቃይ ተሞላ፤ በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ያዘኝ፤ በሰማሁት ነገር ተንገዳገድሁ፤ ባየሁትም ነገር ተሸበርሁ።


እነርሱም እንዲህ አሉት፤ “ሕዝቅያስ እንዲህ ይላል፤ ‘ይህ ቀን የጭንቀት፣ የተግሣጽና የውርደት ቀን ነው፤ ልጆች ሊወለዱ ሲሉ ብርታት እንደሚታጣበት ቀን ሆኗል።


እስኪ ጠይቁ፤ ተመልከቱም፤ ወንድ መውለድ ይችላል? ታዲያ ወንድ ሁሉ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ እጁን በሆዱ ላይ አድርጎ፣ የሰውስ ሁሉ ፊት ጠቍሮ የማየው ለምንድን ነው?


የበኵር ልጇን ለመውለድ እንደምታምጥ፣ በወሊድ እንደምትጨነቅ ሴት ድምፅ ሰማሁ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ትንፋሽ ዐጥሯት ስትጮኽ፣ እጇን ዘርግታ፣ “ወዮልኝ! ተዝለፈለፍሁ፣ በነፍሰ ገዳዮች እጅ ወደቅሁ!” ስትል ሰማሁ።


ስለ እነርሱ ወሬ ደርሶናል፤ ክንዶቻችንም ዝለዋል፤ ጭንቀት ይዞናል፤ እንደምታምጥም ሴት ሆነናል።


ሴት ቀኗ ደርሶ ስትወልድ ትጨነቃለች፤ ከተገላገለች በኋላ ግን፣ ሰው ወደ ዓለም ተወልዷልና ስለ ደስታዋ ጭንቋን ትረሳለች፤


ሰዎች፣ “ሰላምና ደኅንነት ነው” ሲሉ፣ ምጥ እርጉዝ ሴትን እንደሚይዛት እንዲሁ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ ከቶም አያመልጡም።


እርሷም ነፍሰ ጡር ነበረች፤ ልትወልድ ስትል ምጥ ይዟት ተጨንቃ ጮኸች።


跟着我们:

广告


广告