Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 25:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከፍ ብሎ የተመሸገውን ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፤ ወደ ታች ያወርደዋል፤ ወደ ምድር አውርዶም ትቢያ ላይ ይጥለዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የተመሸገውንም ከፍ ከፍ ያለውንም ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፥ ያዋርደማል፤ ትብያ አፈር እስኪሆን ድረስ ይጥለዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የሞአብን ምሽጎች ከታላላቅ ግንቦቻቸው ጋር ያፈራርሳል፤ ተሰባብረውም ከትቢያ ጋር ይቀላቀላሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የተ​መ​ሸ​ገ​ው​ንና ከፍ ከፍ ያለ​ው​ንም ቅጥ​ር​ህን ዝቅ ያደ​ር​ገ​ዋል። ያዋ​ር​ደ​ው​ማል፤ ወደ መሬ​ትም እስከ አፈር ድረስ ይጥ​ለ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የተመሸገውንም ከፍ ከፍ ያለውንም ቅጥርህን ዝቅ ያደርገዋል፥ ያዋርደውማል፥ ወደ መሬትም እስከ አፈር ድረስ ይጥለዋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 25:12
14 交叉引用  

“የጃርት መኖሪያ፣ ረግረጋማ ቦታ አደርጋታለሁ፤ በጥፋትም መጥረጊያ እጠርጋታለሁ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ስለ ሞዓብ የተነገረው ንግር ይህ ነው፤ የሞዓብ ዔር ፈራረሰች፤ በአንድ ሌሊትም ተደመሰሰች። የሞዓብ ቂር ፈራረሰች፣ በአንድ ሌሊት ተደመሰሰች።


ረዣዥሙን ግንብ ሁሉ፣ የተመሸገውን ቅጥር ሁሉ፣


ከተማዪቱን የድንጋይ ክምር አድርገሃታል፤ የተመሸገችውንም ከተማ አፈራርሰሃታል፤ የተመሸገችው የባዕድ ከተማ ከእንግዲህ አትኖርም፤ ተመልሳም አትሠራም።


በከፍታ የሚኖሩትን ዝቅ ዝቅ ያደርጋል፤ ከፍ ከፍ ያለችውን ከተማ ያዋርዳል፤ ወደ ምድር ይጥላታል፤ ከትቢያም ጋራ ይደባልቃታል።


ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ናባው ትጠፋለችና ወዮላት፤ ቂርያታይም ትዋረዳለች፤ ትያዛለችም፤ ምሽጎች ይደፈራሉ፤ ይፈራርሳሉም።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”


እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።


የያዕቆብን መኖሪያ ሁሉ፣ ጌታ ያለ ርኅራኄ ዋጣቸው፤ የይሁዳን ሴት ልጅ ምሽጎች፣ በቍጣው አፈረሳቸው፤ መንግሥቷንና መሳፍንቷን፣ በማዋረድ ወደ ምድር ጣላቸው።


በውበትህ ምክንያት፣ ልብህ ታበየ፤ ከክብርህ ታላቅነት የተነሣም፣ ጥበብህን አረከስህ። ስለዚህ ወደ ምድር ወረወርሁህ፤ ለነገሥታት ትዕይንት አደረግሁህ።


ሕዝቡ የኢያሪኮን ግንብ ሰባት ቀን ከዞሩት በኋላ፣ በእምነት ወደቀ።


ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንሥቶ ወደ ባሕር ወረወረው፤ እንዲህም አለ፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን፣ እንዲህ ባለ ኀይል ትወረወራለች፤ ተመልሳም አትገኝም።


跟着我们:

广告


广告