Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 21:9 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እነሆ፤ አንድ ሰው በፈረሶች በሚሳብ በሠረገላ መጥቷል፤ እንዲህም ሲል መለሰ፣ ‘ባቢሎን ወደቀች፣ ወደቀች! የአማልክቷም ምስሎች ሁሉ፣ ተሰባብረው ምድር ላይ ወደቁ!’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሁነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፦ ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፥ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ጥንድ ጥንድ ሆነው በፈረስ የተቀመጡ ሰዎች እነሆ በድንገት ይመጣሉ፤ ዘብ ጠባቂውም “እነሆ ባቢሎን ወደቀች! የሚሰግዱላቸውም ጣዖቶች ሁሉ ተሰባብረው ወደቁ” የሚል ዜና ያስተላልፋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነ​ሆም፥ በፈ​ረ​ሶች የሚ​ቀ​መጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚ​ሄዱ ፈረ​ሰ​ኞች ይመ​ጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እር​ሱም መልሶ፥ “ባቢ​ሎን ወደ​ቀች! ወደ​ቀች! ጣዖ​ቶ​ች​ዋም ሁሉ፥ የእ​ጆ​ች​ዋም ሥራ​ዎች ሁሉ በም​ድር ላይ ተጥ​ለው ደቀቁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሁነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ ብሎ ጮኸ፥ እርሱም መልሶ፦ ባቢሎን ወደቀች ወደቀች፥ የተቀረጹም የአማልክቶችዋ ምስሎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ አለ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 21:9
22 交叉引用  

የመንግሥታት ዕንቍ፣ የከለዳውያን ትምክሕት የሆነችውን ባቢሎንን፣ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል።


በባቢሎን ንጉሥ ላይ ትሣለቃለህ፤ እንዲህም ትላለህ፤ ጨቋኙ እንዴት አበቃለት! አስገባሪነቱስ እንዴት አከተመ!


ጣዖቶች ሁሉ ፈጽሞ ይወድማሉ።


በፈረሶች የሚሳብ፣ ሠረገሎችን ሲያይ፣ በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣ በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ ያስተውል፤ በጥንቃቄም ያስተውል።”


“አንቺ የባቢሎናውያን ልጅ ሆይ፤ ወደ ጨለማ ግቢ፤ ዝም ብለሽም ተቀመጪ፤ ከእንግዲህ የመንግሥታት እመቤት ተብለሽ አትጠሪም።


እነዚህ ሁለት ነገሮች፣ መበለትነትና የወላድ መካንነት፣ አንድ ቀን ድንገት ይመጡብሻል፤ የቱን ያህል አስማት፣ የቱንም ያህል መተት ቢኖርሽ፣ በሙሉ ኀይላቸው ይመጡብሻል።


“ሁላችሁም በአንድነት ተሰብሰቡ፤ አድምጡም፤ ከጣዖቶች አስቀድሞ እነዚህን የተናገረ ማን ነው? የእግዚአብሔር ምርጥ ወዳጅ የሆነ፣ እርሱ በባቢሎን ላይ ያቀደውን እንዲፈጽም ያደርገዋል፤ ክንዱም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።


“ቀስት የሚገትሩትን፣ ቀስተኞችን ሁሉ በባቢሎን ላይ ጥሩ፤ አንድም ሰው እንዳያመልጥ፣ ዙሪያውን ሁሉ መሽጉ፤ የእስራኤልን ቅዱስ፣ እግዚአብሔርን አቃልላለችና፣ እንደ ሥራዋ መጠን መልሱላት፤ በሌሎች ላይ እንዳደረገችውም አድርጉባት።


ድርቅ በውሆቿ ላይ መጣ! እነሆ፤ ይደርቃሉ፤ ምድሪቱ በፍርሀት በሚሸበሩ አማልክት፣ በጣዖትም ብዛት ተሞልታለችና።


ቀስትና ጦር ይዘዋል፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ በፈረሳቸው እየጋለቡ ሲመጡ፣ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ ያስገመግማል። አንቺ የባቢሎን ሴት ልጅ ሆይ፤ ለጦርነት እንደ ተዘጋጁ ተዋጊዎች ይመጡብሻል።


የታላላቅ መንግሥታትን ማኅበር፣ ከሰሜን በባቢሎን ላይ አስነሣለሁ፤ እነርሱም በርሷ ላይ ይሰለፋሉ፤ መጥተውም ይይዟታል። ቀስቶቻቸው ባዶ እጃቸውን እንደማይመለሱ፣ እንደ ሥልጡን ተዋጊዎች ናቸው።


“በምድር ሁሉ ላይ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ! በሕዝቦች መካከል መለከትን ንፉ! ሕዝቦችን ለጦርነት በርሷ ላይ አዘጋጁ፤ የአራራትን፣ የሚኒንና የአስከናዝን መንግሥታት፣ ጠርታችሁ በርሷ ሰብስቧቸው፤ የጦር አዝማች ሹሙባት፤ ፈረሶችንም እንደ አንበጣ መንጋ ስደዱባት።


ቤልን በባቢሎን ውስጥ እቀጣለሁ፤ የዋጠውን አስተፋዋለሁ፤ ሕዝቦች ከእንግዲህ ወደ እርሱ አይጐርፉም፤ የባቢሎንም ቅጥር ይወድቃል።


የባቢሎንን ጣዖታት የምቀጣበት ጊዜ፣ በርግጥ ይመጣልና። ምድሯ በሙሉ ትዋረዳለች፤ የታረዱትም በሙሉ በውስጧ ይወድቃሉ።


“እንግዲህ ጣዖቶቿን የምቀጣበት ዘመን ይመጣል፤” ይላል እግዚአብሔር፤ “በምድሯም ሁሉ፤ ቍስለኞች ያቃስታሉ።


እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።


ባቢሎን በድንገት ወድቃ ትሰበራለች፤ ዋይ በሉላት! ምናልባት ልትፈወስ ስለምትችል፣ ለቍስሏ የሚቀባ መድኀኒት ፈልጉላት።


ሌላም ሁለተኛ መልአክ፣ “ሕዝቦች ሁሉ፣ የዝሙቷን ቍጣ ወይን ጠጅ እንዲጠጡ ያደረገች ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች!” እያለ ተከተለው።


እርሱም በብርቱ ድምፅ እንዲህ ብሎ ጮኸ፤ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንት መኖሪያ፣ የርኩሳን መናፍስት ሁሉ መጠጊያ፣ የርኩስና የአስጸያፊ ወፎች ሁሉ መጠለያ ሆነች።


ከዚያም አንድ ብርቱ መልአክ፣ ትልቅ የወፍጮ ድንጋይ የሚመስል ድንጋይ አንሥቶ ወደ ባሕር ወረወረው፤ እንዲህም አለ፤ “ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን፣ እንዲህ ባለ ኀይል ትወረወራለች፤ ተመልሳም አትገኝም።


跟着我们:

广告


广告