Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 21:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጠባቂው ጮኸ፤ እንዲህም አለ፤ “ጌታ ሆይ፤ በየቀኑ ማማ ላይ ቆሜአለሁ፤ በየሌሊቱም በቦታዬ አለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ያየውም፦ ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ዘብ ጠባቂው “ጌታዬ ሆይ! እኔ በማማዬ ላይ ሆኜ ሌት ከቀን በመጠበቅ ላይ ነኝ” ይላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጕበኛ ኦር​ያስ ተጠራ፤ እር​ሱም፥ “እነሆ እኔ አለሁ፤ መላ መዓ​ል​ቱ​ንና መላ ሌሊ​ቱን በማማ ላይ ቆሜ አለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ያየውም፦ ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፥

参见章节 复制




ኢሳይያስ 21:8
12 交叉引用  

የይሁዳ ሰዎች ምድረ በዳውን ቍልቍል ወደሚያሳየው ቦታ መጥተው ግዙፉን ሰራዊት ሲመለከቱ፣ መሬቱ ሬሳ በሬሳ ሆኖ አዩ፤ አንድም ሰው አላመለጠም።


እግዚአብሔር ቤትን ካልሠራ፣ ሠራተኞች በከንቱ ይደክማሉ፤ እግዚአብሔር ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል።


በመኝታዬ ዐስብሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ ስለ አንተ አሰላስላለሁ።


ጩኸታቸው እንደ አንበሳ ነው፤ እንደ አንበሳ ደቦል ያገሣሉ፤ ያደኑትንም ይዘው ይጮኻሉ፤ ተሸክመውት ይሄዳሉ፤ የሚያስጥልም የለም።


የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ተጋድመው ያልማሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።


ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ዘብ ጠባቂዎችን በቅጥሮችሽ ላይ አቁሜአለሁ፤ ቀንም ሆነ ሌሊት ፈጽሞ አይታክቱም። እናንተ ወደ እግዚአብሔር አቤት፣ አቤት የምትሉ፤ ፈጽሞ አትረፉ፤


እንደ አንበሳ ከጐሬው ይወጣል፤ ከአስጨናቂው ሰይፍ፣ ከቍጣውም የተነሣ፣ ምድራቸው ባድማ ትሆናለች።


አንበሳ ከደኑ ወጥቷል፤ ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቷል፤ ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ ከስፍራው ወጥቷል። ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።


“አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም በኤዶም ላይ ድንገት እወጣለሁ፤ ከምድሩም አባርረዋለሁ። የመረጥሁትን በርሱ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”


አንበሳ ከዮርዳኖስ ደኖች ድንገት ወጥቶ፣ ወደ ግጦሽ ሜዳ ብቅ እንደሚል፣ እኔም ባቢሎንን ሳይታሰብ ከምድሯ አባርራታለሁ፤ የመረጥሁትንም በርሷ ላይ እሾማለሁ፤ እንደ እኔ ያለ ማን ነው? ማንስ ሊገዳደረኝ ይችላል? የትኛውስ እረኛ ሊቋቋመኝ ይችላል?”


ራሳችሁን የምትገዙ ሁኑ፣ ንቁም፤ ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ወዲያ ወዲህ ይዞራልና።


跟着我们:

广告


广告