Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር አውራ መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራውያን ወደ ግብጽ፣ ግብጻውያንም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብጻውያንና አሦራውያን በአንድነት ያመልካሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይዘረጋል፤ አሦራዊያንም ወደ ግብጽ፥ ግብፃዊውም ወደ አሦር ይሄዳሉ፤ ግብፃውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚያን ጊዜ በግብጽና በአሦር መካከል አውራ ጎዳና ይከፈታል፤ የእነዚህ ሁለት አገር ሕዝቦች አንዱ ወገን ወደ ሌላ ይተላለፋሉ፤ የሁለቱም ሕዝቦች አምልኮ አንድ ዐይነት ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በዚ​ያም ወራት ከግ​ብፅ ወደ አሦር መን​ገድ ይሆ​ናል፤ አሦ​ራ​ዊ​ውም ወደ ግብፅ፥ ግብ​ፃ​ዊ​ውም ወደ አሦር ይገ​ባል፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ለአ​ሦ​ራ​ው​ያን ይገ​ዛሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በዚያ ቀን ከግብጽ ወደ አሦር መንገድ ይሆናል፥ አሦራዊውም ወደ ግብጽ፥ ግብጻዊውም ወደ አሦር ይገባል፥ ግብጻውያንም ከአሦራውያን ጋር ይሰግዳሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:23
15 交叉引用  

“ከሚያውቁኝ መካከል፣ ረዓብንና ባቢሎንን እጠቅሳለሁ፤ እነሆ፤ ፍልስጥኤምና ጢሮስ ከኢትዮጵያ ጋራ፣ ‘ይህ ሰው በዚያ ነው የተወለደው’ ይላሉ።”


በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


እስራኤል ከግብጽ በወጣ ጊዜ እንደ ሆነው ሁሉ፣ ከአሦር ለተረፈው ቅሬታ ሕዝብ፣ እንዲሁ ጐዳና ይዘጋጅለታል።


በዚያ ቀን እስራኤል፣ ከግብጽና ከአሦር ጋራ የምድር በረከት ለመሆን በሦስተኛነት ትቈጠራለች።


ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።


በዚያ ቀን ታላቅ መለከት ይነፋል፤ በአሦር የጠፉትና በግብጽ የተሰደዱትም መጥተው፣ በተቀደሰው ተራራ በኢየሩሳሌም እግዚአብሔርን ያመልካሉ።


ተራሮቼን ሁሉ መንገድ አደርጋለሁ፤ ጐዳናዎቼም ከፍ ይላሉ።


እግዚአብሔር፣ ታዳጊ የሆነው የእስራኤል ቅዱስ፣ ለተናቀውና በሕዝብ ለተጠላው፣ የገዦች አገልጋይ እንዲህ ይላል፤ “ነገሥታት አይተውህ ይነሣሉ፤ ልዑላንም አይተው ይሰግዳሉ፤ ምክንያቱም የመረጠህ የእስራኤል ቅዱስ፣ እግዚአብሔር ታማኝ ነው።”


ዕለፉ፤ በበሮቹ በኩል ዕለፉ፤ ለሕዝቡ መንገድ አዘጋጁ፤ አስተካክሉ፤ ጐዳናውን አስተካክሉ! ድንጋዩን አስወግዱ፤ ለመንግሥታትም ምልክት አሳዩ።


“ከአንዱ ወር መባቻ እስከ ሌላው፣ እንዲሁም ከአንዱ ሰንበት እስከ ሌላው፣ የሰው ልጅ ሁሉ በፊቴ ሊሰግድ ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር፤


በዚያ ቀን ሰዎች፣ ከአሦር እስከ ግብጽ ከተሞች፣ ከግብጽ እስከ ኤፍራጥስ፣ ከባሕር ወደ ባሕር፣ ከተራራ ወደ ተራራ ወደ እናንተ ይመጣሉ።


跟着我们:

广告


广告