Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 የይሁዳ ምድር በግብጽ ላይ ሽብር ትነዛለች፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ካቀደው የተነሣ፣ ስለ ይሁዳ ወሬ የሰማ ሁሉ ይሸበራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የይሁዳም ምድር ለግብጽ ሽብር ትሆናለች፤ የሠራዊት ጌታ ከመከረባት ምክር የተነሣ ወሬዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ይሁዳ ለግብጽ ሕዝብ አስፈሪ ትሆናለች፤ የይሁዳ ስም ሲነሣ እንኳ በጣም ይሸበራሉ፤ ይህም የሚሆነው የሠራዊት አምላክ እነርሱን ለመቅጣት መዘጋጀቱን በማወቃቸው ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 የይ​ሁ​ዳም ምድር ግብ​ፅን የም​ታ​ስ​ደ​ነ​ግጥ ትሆ​ና​ለች፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከመ​ከ​ረ​ባት ምክር የተ​ነሣ ስም​ዋን የሚ​ሰማ ሁሉ ይፈ​ራል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 የይሁዳም ምድር ግብጽን የምታስደነግጥ ትሆናለች፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከመከረባት ምክር የተነሣ ወሬዋን የሚሰማ ሁሉ ይፈራል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:17
12 交叉引用  

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል።


ንጉሥ ሕዝቅያስ በነገሠ በዐሥራ አራተኛው ዓመት፣ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም የተመሸጉትን የይሁዳ ከተሞች ሁሉ አጥቅቶ ያዛቸው።


የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን፣ አገልጋዮቹን፣ ባለሥልጣኖቹንና ሕዝቡን ሁሉ፣


“ ‘በዚያ ቀን ከእኔ ዘንድ መልእክተኞች በመርከብ ወጥተው ያለ ሥጋት ከተቀመጠችበት ሁኔታ ለማውጣት ኢትዮጵያን ያስፈራሯታል፤ ግብጽ በጨለማ በምትዋጥበት ቀን ጭንቅ ይይዛቸዋል፤ ቀኑ በርግጥ ይመጣልና።


የምድር ሕዝቦች ሁሉ፣ እንደ ኢምንት ይቈጠራሉ፤ በሰማይ ኀይላት፣ በምድርም ሕዝቦች ላይ፣ የወደደውን ያደርጋል፤ እጁን መከልከል የሚችል የለም፤ “ምን ታደርጋለህ?” ብሎ የሚጠይቀውም የለም።


跟着我们:

广告


广告