Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 19:12 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 የእናንተ ጠቢባን አሁን የት አሉ? የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብጽ ላይ ያሰበውን ነገር፣ እስኪ ያሳዩአችሁ፤ ያሳውቋችሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 አሁንስ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፤ የሠራዊት ጌታ በግብጽ ላይ ያሰበውን ይወቁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የግብጽ ንጉሥ ሆይ! እነዚያ ብልኆች አማካሪዎችህ የት አሉ? የሠራዊት አምላክ በግብጽ ላይ ያቀደውን ይንገሩህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 አሁን ጥበ​በ​ኞ​ችህ የት አሉ? አሁን ያብ​ስ​ሩህ፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በግ​ብፅ ላይ ያሰ​በ​ውን እስኪ ይን​ገ​ሩህ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 አሁንሳ ጥበበኞችህ የት አሉ? አሁን ይንገሩህ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በግብፅ ላይ ያሰበውን ይወቁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 19:12
13 交叉引用  

የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ምሏል፤ “እንደ ዐቀድሁት በርግጥ ይከናወናል፤ እንደ አሰብሁትም ይሆናል።


እስኪ እንደ እኔ ማን አለ? ይናገር፤ ሕዝቤን ከጥንት ስመሠርት ምን እንደ ነበረ፣ ገና ወደ ፊት ምን እንደሚሆን፣ ይናገር፤ በፊቴ ያስረዳ፤ ስለሚመጣውም ነገር አስቀድሞ ይናገር።


ራሳቸውን እንደ ብልኅ ለሚቈጥሩ፣ በራሳቸውም አመለካከት ጥበበኛ ለሆኑ ወዮላቸው!


ታዲያ፣ ልታመልካቸው ያበጀሃቸው አማልክት ወዴት ናቸው? በመከራህ ጊዜ ሊያድኑህ የሚችሉ ከሆነ፣ ይሁዳ ሆይ፤ እስኪ ይምጡና ያድኑህ፤ የከተሞችህን ቍጥር ያህል፣ የአማልክትህም ብዛት እንዲሁ ነውና።


“በዚያ ቀን ጥበበኛ ሰዎችን ከኤዶም፣ አስተዋዮችንም ከዔሳው ተራሮች አልደመስስምን?” ይላል እግዚአብሔር።


መጽሐፍ ፈርዖንን፣ “ኀይሌ በአንተ እንዲታይ፣ ስሜም በምድር ሁሉ እንዲታወቅ ለዚህ አስነሣሁህ” ይላልና።


ጠቢብ የት አለ? ሊቅስ የት አለ? የዘመኑስ ፈላስፋ የት አለ? እግዚአብሔር የዓለምን ጥበብ ሞኝነት አላደረገምን?


ከዚያም ዜቡል፣ “እንገዛለት ዘንድ አቢሜሌክ ማን ነው? ብለህ የደነፋኸው አሁን የት አለ? ያቃለልሀቸውስ ሰዎች እነዚህ አይደሉምን? በል ውጣና ግጠማቸው” አለው።


跟着我们:

广告


广告