Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ከድኻም ድኻ የሆኑት መሰማሪያ ያገኛሉ፤ ችግረኞችም ያለ ሥጋት ይተኛሉ፤ ሥርህን ግን በራብ እገድላለሁ፤ ትሩፋንህንም እፈጃለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 የድሆችም የበኩር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፤ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 እጅግ የደኸዩ መጠጊያ ያገኛሉ፤ ድኽነት ያጠቃቸውም ተዝናንተው ይኖራሉ፤ የእናንተን ልጆች ግን በራብ እገድላለሁ፤ የተረፋችሁትንም አጠፋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ድሆ​ችም በው​ስ​ጣ​ችሁ ይሰ​ማ​ራሉ፤ ድሆች ሰዎ​ችም በሰ​ላም ያር​ፋሉ፤ ዘራ​ች​ሁ​ንም ረኃብ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ ከእ​ና​ን​ተም የቀ​ሩት ያል​ቃሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 የድሆችም የበኵር ልጆች ይሰማራሉ፥ ችግረኞችም ተዘልለው ይተኛሉ፥ ሥርህንም በራብ እገድላለሁ፥ ቅሬታህም ይገደላል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:30
21 交叉引用  

ደዌ ቈዳውን ይበላል፤ የሞት በኵርም ቅልጥሙን ይውጣል።


ነገር ግን ለድኾች በጽድቅ ይፈርዳል፤ ለምድር ምስኪኖችም ፍትሕን ይበይናል፤ በአፉ በትር ምድርን ይመታል፤ በከንፈሩም እስትንፋስ ክፉዎችን ይገድላል።


ትሑታን በእግዚአብሔር፣ ምስኪኖችም በእስራኤል ቅዱስ እንደ ገና ሐሤት ያደርጋሉ።


እግዚአብሔር፣ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋራ እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤


ሕዝቤን በችግር ስታደቅቁት፣ የድኾችንም ፊት በሐዘን ስታገረጡት ምን ማለታችሁ ነው?” ይላል ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።


“ሕዝቅያስ ሆይ፤ ይህ ምልክት ይሆንልሃል፤ “በዚህ ዓመት የገቦውን፣ በሚቀጥለው ዓመት ከገቦው የበቀለውን ትበላላችሁ፤ በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ ወይን ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።


በጎችም በገዛ መሰማሪያቸው እንደሚሰማሩ ሆነው ይግጣሉ፤ የበግ ጠቦቶችም በባለጠጎች ፍርስራሽ ላይ ሣር ይበላሉ።


እነሆ፤ በጥፋት ላይ ጥፋት መጥተውብሻል፤ ታዲያ ማን ያጽናናሻል? እነርሱም መፈራረስና ጥፋት፣ ራብና ሰይፍ ናቸው፤ ታዲያ ማን ያስተዛዝንሽ?


ተጨንቀውና ተርበው በምድሪቱ ላይ ይንከራተታሉ፤ ክፉኛ ሲራቡም ይቈጣሉ፤ ወደ ላይ እየተመለከቱ ንጉሣቸውንና አምላካቸውን ይራገማሉ።


በቀኝ በኩል ይጐርሳሉ፤ ነገር ግን ራባቸው አይታገሥም፤ በግራም በኩል ይበላሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ እያንዳንዱም የገዛ ወገኑን ሥጋ ይበላል።


በእግዚአብሔር ስም የሚታመኑትን፣ የዋሃንንና ትሑታንን፣ በመካከላችሁ አስቀራለሁ።


跟着我们:

广告


广告