Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 13:2 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፣ በእጅ ምልክት ስጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፤ በእጅ ምልክት ስጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ምንም ነገር በማይበቅልበት ተራራ ጫፍ ሆናችሁ ምልክት ስጡ፤ ወደ ትዕቢተኞቹ የባቢሎን ገዢዎች ወደሚያስገባው በር እንዲገቡ ትእዛዝ ስጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምል​ክ​ትን አቁሙ፤ ድም​ፃ​ች​ሁ​ንም ከፍ አድ​ር​ጉ​ባ​ቸው፤ አለ​ቆች በእጅ ጥቀሱ። በሮ​ች​ንም ክፈቱ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ምድረ በዳ በሆነ ተራራ ላይ ምልክትን አቁሙ፥ ድምፅንም ከፍ አድርጉባቸው፥ በአለቆችም ደጆች እንዲገቡ በእጅ ጥቀሱ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 13:2
15 交叉引用  

ነገር ግን ከቀስት እንዲያመልጡ፣ ለሚፈሩህ ምልክት አቆምህላቸው። ሴላ


በዚህ ቀን ኖብ ይደርሳሉ፤ እጃቸውን በኢየሩሳሌም ኰረብታ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ተራራ ላይ በዛቻ ነቀነቁ።


ለመንግሥታት ምልክትን ያቆማል፤ ከእስራኤልም የተሰደዱትን መልሶ ያመጣቸዋል፤ የተበተኑትን የይሁዳ ሕዝብ፣ ከአራቱ የምድር ማእዘን ይሰበስባል።


እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ።


እናንተ የዓለም ሕዝቦች፣ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ፣ በተራሮች ላይ ምልክት ሲሰቀል ታዩታላችሁ፤ መለከትም ሲነፋ ትሰሙታላችሁ።


በዚያ ቀን ግብጻውያን እንደ ሴት ይሆናሉ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ በሚያንቀሳቅሰው ክንዱ ፊት ይፈራሉ፤ ይንቀጠቀጣሉም።


ጠንካራ ምሽጉ በሽብር ምክንያት ይወድቃል፤ መሪዎቹም የጦር ዐርማ ሲያዩ በድንጋጤ ይዋጣሉ” ይላል እሳቱ በጽዮን፣ ማንደጃውም በኢየሩሳሌም የሆነ እግዚአብሔር።


ከሩቅ ያሉትን ሕዝቦች የሚጠራበትን ምልክት ያቆማል፤ ከምድር ዳርቻም በፉጨት ይጠራቸዋል፤ እነርሱም እየተጣደፉ በፍጥነት ይመጣሉ።


“በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’


“እነሆ፤ ሰራዊት ከሰሜን ይመጣል፤ አንድ ኀያል መንግሥትና ብዙ ነገሥታት፣ ከምድር ዳርቻ ተነሣሥተዋል።


በባቢሎን ቅጥር ላይ ዐላማ አንሡ ጥበቃውን አጠናክሩ፤ ዘብ ጠባቂዎችን አቁሙ፤ ደፈጣ ተዋጊዎችን አዘጋጁ እግዚአብሔር በባቢሎን ሕዝብ ላይ የወሰነውን፣ ዐላማውን ያከናውናል።


“አንቺ ምድርን ሁሉ ያጠፋሽ፣ አጥፊ ተራራ ሆይ፤ እኔ በአንቺ ላይ ነኝ፣” ይላል እግዚአብሔር፤ “እጄን በአንቺ ላይ አነሣለሁ፤ ከገመገም ቍልቍል አንከባልልሻለሁ፤ የተቃጠለም ተራራ አደርግሻለሁ።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”


跟着我们:

广告


广告