ኢሳይያስ 11:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም15 እግዚአብሔር በሚጋረፍም ነፋስ፣ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ጌታ በሚጋረፍም ነፋስ የግብጽን ባሕረ ሰላጤ ያደርቃል፤ እጁን በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ ይዘረጋል፤ ሰባት ታናናሽ ጅረትም አድርጎ ይለያየዋል፤ ስለዚህ ሰዎች ከነጫማቸው መሻገር ይችላሉ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 እግዚአብሔር የግብጽን ባሕረ ልሳን ያደርቃል፤ ማንም ሰው በእግሩ መሻገር እንዲችል የኤፍራጥስን ወንዝ በኀይለኛ ነፋስ መትቶ ወደ ትናንሽ ሰባት ጅረቶች ይከፋፍለዋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 እግዚአብሔርም የግብፅን ባሕር ያደርቃል፤ በኀይለኛም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፤ ሰባት ፈሳሾችንም ይመታል፤ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 እግዚአብሔርም የግብጽን ባሕር ያጠፋል፥ በትኩሱም ነፋስ እጁን በወንዙ ላይ ያነሣል፥ ሰባት ፈሳሾችንም አድርጎ ይመታዋል፥ ሰዎችም በጫማቸው እንዲሻገሩ ያደርጋቸዋል። 参见章节 |