Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ ቢሆንም፣ ትሩፉ ብቻ ይመለሳል። ጽድቅ የሰፈነበት ጥፋት ታውጇል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፤ የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ። ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ምንም እንኳ የእስራኤል ሕዝብ ብዛት እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ቢሆንም ከእነርሱ መካከል የሚድኑት የተረፉት ብቻ ናቸው፤ ለሕዝቡ ጥፋት ተገቢ የሆነ እውነተኛ ፍርድ ተዘጋጅቶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሕዝብ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን የቀ​ሩት ይድ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እስራኤል ሆይ፥ የሕዝብህ ቍጥር እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆን ቅሬታው ይመለሳል። ጽድቅ የተትረፈረፈበትም ጥፋት ተወስኖአል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:22
24 交叉引用  

እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”


የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር።


ቅሬታ የሆኑት ከኢየሩሳሌም፣ የተረፉትም ከጽዮን ተራራ ይመጣሉና። የሰራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ያደርጋል።


እንደ ገናም የይሁዳ ቤት ቅሬታ፣ ሥሩን ወደ ታች ይሰድዳል፤ ከላይም ፍሬ ያፈራል፤


“እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ።


ዘርህ እንደ አሸዋ፣ ልጆችህ ስፍር እንደሌለው ትቢያ በሆኑ ነበር፤ ስማቸው አይወገድም፤ ከፊቴም አይጠፋም።”


“አዳኝ ወደ ጽዮን፣ ኀጢአታቸውንም ወደ ተናዘዙት ወደ ያዕቆብ ቤት ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር።


እኔም፣ “ጌታ ሆይ፤ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?” አልሁት። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፤ “ከተሞች እስኪፈራርሱና የሚኖሩባቸው እስኪያጡ፣ ቤቶችም ወና እስኪሆኑና ምድርም ፈጽሞ ባድማ እስክትሆን ድረስ፤


ከዐሥር አንድ ሰው እንኳ በምድሪቱ ቢቀር፣ እርሱም ደግሞ ይጠፋል፤ ነገር ግን የኮምበልና የወርካ ዛፍ በተቈረጠ ጊዜ ጕቶ እንደሚቀር፣ ቅዱሱም ዘር እንዲሁ በምድሪቱ ጕቶ ሆኖ ይቀራል።”


ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺሕ፣ ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በወይኑ ዘለላ ውስጥ ጭማቂው ገና እንዳለ ሁሉ፣ ሰዎችም፣ ‘በውስጡ በረከት ስላለ አትቍረጡት’ እንደሚሉ፣ እኔም ስለ ባሮቼ ስል እንዲሁ አደርጋለሁ፤ ሙሉ በሙሉ አላጠፋቸውም።


እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።”


“ከዳተኛ ልጆች ሆይ፤ እኔ ባለቤታችሁ ነኝና ተመለሱ” ይላል እግዚአብሔር፤ “ከአንድ ከተማ አንድ፣ ከአንድ ነገድ ሁለት መርጫችሁ ወደ ጽዮን አመጣችኋለሁ።


ከሰይፍ አምልጠው፣ ከግብጽ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመለሱት በጣም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። በግብጽ ምድር ለመኖር የመጡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ፣ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማንኛችን ቃል እንደሚጸና ያውቃሉ።


አለቃው ከብዙዎች ጋራ ለአንድ ሱባዔ ቃል ኪዳኑን ያጸናል፤ በሱባዔውም እኵሌታ መሥዋዕትና ቍርባን ማቅረብን ያስቀራል። የታወጀው ፍርድ በርሱ ላይ እስኪፈስስ ድረስ፣ ጥፋትን የሚያመጣ የጥፋት ርኩሰት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያቆማል።”


“ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ሊሰፈርና ሊቈጠር እንደማይችል እንደ ባሕር አሸዋ ይሆናሉ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ በተባሉበት ቦታ፣ ‘የሕያው አምላክ ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።


በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ላይ በጽድቅ የሚፈርድበትን ቀን ወስኗልና፤ እርሱንም ከሙታን በማስነሣቱ ለሰዎች ሁሉ ይህን አረጋግጧል።”


ነገር ግን በድንዳኔህና ንስሓ በማይገባ ልብህ ምክንያት ትክክለኛ ፍርዱ ሲገለጥ በእግዚአብሔር የቍጣ ቀን በራስህ ላይ ቍጣን ታከማቻለህ።


በአራቱ የምድር ማእዘናት ያሉትን ሕዝቦች፣ ጎግንና ማጎግን እያሳተ ለጦርነት ሊያሰልፋቸው ይወጣል። ቍጥራቸው በባሕር ዳርቻ እንዳለ አሸዋ ነው።


跟着我们:

广告


广告