Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 1:14 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የወር መባቻችሁንና በዓላታችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፤ መታገሥም አልቻልሁም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የወር መባቻችሁንና የተደነገጉ በዓሎቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ ሸክም ሆነውብኛል፤ መታገሥም አልቻልሁም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አዲስ ጨረቃ የምትወጣበትን የወር መባቻችሁንና በዓሎቻችሁን ጠልቻለሁ፤ እነርሱ እንደ ከባድ ሸክም ስለ ሆኑብኝ ልታገሣቸው አልችልም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 መባ​ቻ​ች​ሁ​ንና በዓ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ነፍሴ ጠል​ታ​ለች፤ አስ​ጸ​ያፊ ሆና​ች​ሁ​ብ​ኛል፤ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁ​ንም ይቅር አል​ልም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፥ ሸክም ሆነውብኛል፥ ልታገሳቸውም ደክሜያለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 1:14
13 交叉引用  

እንዲሁም በየሰንበቱ፣ በወር መባቻ በዓልና በተደነገጉት በዓላት ሁሉ፣ የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በሚቀርብበት ጊዜ ይፈጽሙ ነበር፤ በተወሰነላቸው ቍጥርና በተሰጠውም መመሪያ መሠረት፣ ዘወትር በእግዚአብሔር ፊት ያገለግሉ ነበር።


ዳዊት የሰፈረብሽ ከተማ፣ አርኤል፣ አርኤል ወዮልሽ! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሪ፣ ዐውደ ዓመትሽም ይቀጥል።


ነገር ግን አርኤልን እከብባለሁ፤ ታለቅሳለች፤ ዋይ ዋይ ትላለች፤ ለእኔም እንደ መሠዊያ ስፍራ ትሆንልኛለች።


መልካም መዐዛ ያለው ከሙን አልገዛህልኝም፤ በመሥዋዕትህ ሥብ አላጠገብኸኝም፤ ነገር ግን በኀጢአትህ አስቸገርኸኝ፤ በበደልህም አደከምኸኝ።


“እኔ እግዚአብሔር ፍትሕን ስለምወድድ፣ ዝርፊያንና በደልን እጠላለሁ፤ በታማኝነቴም የሚገባቸውን እሰጣቸዋለሁ፤ ከእነርሱም ጋራ የዘላለም ኪዳን አደርጋለሁ።


“ከአንዱ ወር መባቻ እስከ ሌላው፣ እንዲሁም ከአንዱ ሰንበት እስከ ሌላው፣ የሰው ልጅ ሁሉ በፊቴ ሊሰግድ ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር፤


ኢሳይያስም እንዲህ አለ፤ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፤ ስሙ! የሰውን ትዕግሥት መፈታተናችሁ አንሶ የአምላኬን ትዕግሥት ትፈታተናላችሁን?


የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣ የዓመት በዓላቷንና የወር መባቻዎቿን፣ ሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓላቷን ሁሉ አስቀራለሁ።


ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ ዲቃሎች ወልደዋልና፤ ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤ እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል።


“እነሆ፤ በእህል የተሞላ ጋሪ እንደሚያደቅቅ፣ እኔም አደቅቃችኋለሁ።


“ዓመት በዓላችሁን ተጸይፌአለሁ፤ ጠልቼውማለሁ፤ ጉባኤዎቻችሁ ደስ አያሰኙኝም።


በአንድ ወር ውስጥ ሦስቱን እረኞች አስወገድሁ። በጎቹ ጠሉኝ፤ እኔም፣ ሰለቸኋቸው፤


እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችሁታል። እናንተም፣ “ያታከትነው እንዴት ነው?” ትላላችሁ? “ክፉ የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነው፤ እርሱም በክፉዎች ደስ ይለዋል” ወይም “የፍትሕ አምላክ ወዴት ነው?” በማለታችሁ ነው።


跟着我们:

广告


广告