Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 7:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 እኔ አሠለጠንኋቸው፤ አጠነከርኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐደሙብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ክንዳቸውን ያስተማርሁና ያጸናሁ እኔ ነበርሁ፤ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን አሴሩብኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ያሠለጠንኳቸውና ጒልበታቸው አንዲጠነክር ያደረግኹ እኔ ነኝ፤ እነርሱ ግን በእኔ ላይ ያሤራሉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 በእ​ኔም ዘንድ ተገ​ሠጹ፤ እኔም ክን​ዳ​ቸ​ውን አጸ​ናሁ፤ እነ​ርሱ ግን ክፉ ነገ​ርን መከ​ሩ​ብኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እኔም ክንዳቸውን አስተማርሁና አጸናሁ፥ እነርሱ ግን ክፉ ነገርን መከሩብኝ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 7:15
18 交叉引用  

እግዚአብሔር ግን ራራላቸው፤ ዐዘነላቸው፤ ፊቱን መለሰላቸው፤ ይህም ከአብርሃም፣ ከይሥሐቅና ከያዕቆብ ጋራ ስለ ገባው ኪዳን ሲል ነው፤ እስከ ዛሬ ድረስ ሊያጠፋቸው አልፈለገም፤ ከፊቱም አላስወገዳቸውም።


ስለዚህ እግዚአብሔር ለእስራኤል የሚታደጋቸውን ሰው ሰጠ፤ እነርሱም ከሶርያውያን ጭቈና ተላቀቁ፤ እንደ ቀድሞውም በየድንኳናቸው መኖር ጀመሩ፤


“እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ብፁዕ ነው፤ ስለዚህ ሁሉን ቻይ አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።


እነርሱ በልባቸው ክፉ ነገር ያውጠነጥናሉ፤ በየዕለቱም ጦርነት ይጭራሉ።


አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ?


ሰውን የምታጠቁት እስከ መቼ ነው? ይህን የዘመመ ግድግዳ፣ የተንጋደደ ዐጥር፣ ሁላችሁ ገፍታችሁ ልትጥሉት ትሻላችሁ?


ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣ ከሕግህም የምታስተምረው ሰው፤


ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በዘለፋውም አትመረር፤


የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ ነው፤ ፈውስም የለውም፤ ማንስ ሊረዳው ይችላል?


“እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣ ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።


በእግዚአብሔር ላይ ምንም ቢያሤሩ፣ እርሱ ያጠፋዋል፤ መከራም ዳግመኛ አይነሣም።


በመንፈስ ቅዱስም አማካይነት በብላቴናህ በአባታችን በዳዊት አፍ እንዲህ ብለህ ተናግረሃል፤ “ ‘አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ?


እግዚአብሔርን ቢያውቁም እንኳ፣ እንደ አምላክነቱ አላከበሩትም፤ ምስጋናም አላቀረቡለትም፤ ነገር ግን ሐሳባቸው ፍሬ ቢስ ሆነ፤ የማያስተውል ልባቸው ጨለመ።


በእግዚአብሔር ዕውቀት ላይ በትዕቢት የሚነሣውን ክርክርና ከንቱ ሐሳብ ሁሉ እናፈርሳለን፤ አእምሮንም ሁሉ እየማረክን ለክርስቶስ እንዲታዘዝ እናደርጋለን።


ልጆች እንደ መሆናችሁ እንዲህ በማለት የተናገራችሁን ማበረታቻ ቃልም ረስታችኋል፦ “ልጄ ሆይ፤ የጌታን ተግሣጽ አታቃልል፤ በሚቀጣህም ጊዜ ተስፋ አትቍረጥ፤


እኔ የምወድዳቸውን እገሥጻለሁ፤ እቀጣለሁም። ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ።


跟着我们:

广告


广告