Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሆሴዕ 2:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ምድርም ለእህል፣ ለአዲስ የወይን ጠጅና ለዘይት ምላሽ ትሰጣለች፤ እነርሱም ለኢይዝራኤል ምላሽ ይሰጣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ለእኔም እንድትሆኚ በታማኝነት አጭሻለሁ፤ አንቺም ጌታን ታውቂአለሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ምድርም እህልን፥ ወይንንና የወይራ ዘይትን በማስገኘት ለኢይዝራኤል መልስ ትሰጣለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ምድ​ርም ለእ​ህል፥ ለወ​ይ​ንና ለዘ​ይት ትመ​ል​ሳ​ለች፤ እነ​ር​ሱም ለኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ይመ​ል​ሳሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ለእኔም እንድትሆኚ በመታመን አጭሻለሁ፥ አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂአለሽ።

参见章节 复制




ሆሴዕ 2:22
8 交叉引用  

ከእንግዲህ፣ “የተተወች” ብለው አይጠሩሽም፤ ምድርሽም፣ “የተፈታች” አትባልም፤ ነገር ግን፣ “ደስታዬ በርሷ” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፣ “ባለባል” ትባላለች፤ እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ይለዋል፤ ምድርሽም ባለባል ትሆናለች።


እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹም ልባቸውም ወደ እኔ ስለሚመለሱ፣ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣ በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣ በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ ከእንግዲህም አያዝኑም።


የይሁዳ ሕዝብና የእስራኤል ሕዝብ እንደ ገና አንድ ይሆናሉ፤ አንድ መሪም ይሾማሉ፤ አንድ ሆነውም በምድሪቱ ይገንናሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።


እግዚአብሔርም ሆሴዕን እንዲህ አለው፤ “በኢይዝራኤል ስለ ተፈጸመው ግድያ የኢዩን ቤት በቅርቡ ስለምቀጣና የእስራኤልንም መንግሥት እንዲያከትም ስለማደርግ፣ ስሙን ኢይዝራኤል ብለህ ጥራው።


ሰዎች እንደ ገና ከጥላው በታች ያርፋሉ፤ እርሱም እንደ እህል ይለመልማል፤ እንደ ወይን ተክል ያብባል፤ ዝናውም እንደ ሊባኖስ የወይን ጠጅ ይወጣል።


እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ይመልስላቸዋል፤ “እህል፣ አዲስ የወይን ጠጅና ዘይት፣ እስክትጠግቡ ድረስ እሰጣችኋለሁ፤ የሕዝቦች መዘባበቻ አላደርጋችሁም።


በኢየሩሳሌም እንዲኖሩ መልሼ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በጽድቅና በታማኝነት አምላካቸው እሆናለሁ።”


跟着我们:

广告


广告