Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 13:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በእስር ላይ ያሉትን ከእነርሱ ጋራ እንደ ታሰራችሁ ሆናችሁ አስቧቸው፤ እንዲሁም በሰው እጅ የሚንገላቱትን ራሳችሁ መከራ እንደምትቀበሉ አድርጋችሁ አስቧቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 እስረኞችን አብራችኋቸው እንደታሰረ ሆናችሁ አስቡ፤ እናንተም በሥጋ እንዳለ እያሰባችሁ የተጨነቁትንም እንደራሳችሁ አስቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከእነርሱ ጋር አብራችሁ እንደ ታሰራችሁ ያኽል ሆናችሁ እስረኞችን አስታውሱ፤ እናንተም እንደ እነርሱ መከራ የምትቀበሉ ያኽል ሆናችሁ መከራ የሚቀበሉትን አስቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ከእ​ነ​ርሱ ጋር አብ​ራ​ች​ኋ​ቸው እንደ ታሰ​ራ​ችሁ ሆና​ችሁ እስ​ረ​ኞ​ችን ዐስቡ፤ መከራ የጸ​ና​ባ​ቸ​ው​ንም በሥ​ጋ​ችሁ ከእ​ነሱ ጋር እን​ዳ​ላ​ችሁ ሆና​ችሁ ዐስቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ከእነርሱ ጋር እንደ ታሰረ ሆናችሁ እስሮችን አስቡ፥ የተጨነቁትንም ራሳችሁ ደግሞ በሥጋ እንዳለ ሆናችሁ አስቡ።

参见章节 复制




ዕብራውያን 13:3
19 交叉引用  

የሆነው ሆኖ፣ የመጠጥ አሳላፊዎቹ አለቃ ዮሴፍን አላስታወሰውም፤ ረሳው እንጂ።


ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ አስታምማችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’


እንግዳ ሆኜ አልተቀበላችሁኝም፤ ታርዤ አላለበሳችሁኝም፤ ታምሜና ታስሬ አልጠየቃችሁኝም።’


ከዚያም ለጳውሎስ መጠነኛ ነጻነት እየሰጠ እንዲጠብቀውና ወዳጆቹም ገብተው እንዲያገለግሉት ፈቃድ ይሰጣቸው ዘንድ የመቶ አለቃውን አዘዘው።


በሚቀጥለው ቀን ሲዶና ደረስን፤ ዩልዮስም ለጳውሎስ ደግነት በማሳየት ወደ ወዳጆቹ ሄዶ ርዳታ እንዲቀበል ፈቀደለት።


ደስ ከሚላቸው ጋራ ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያዝኑም ጋራ ዕዘኑ።


አንድ ብልት ቢሠቃይ፣ ብልቶች ሁሉ ዐብረው ይሠቃያሉ፤ አንድ ብልት ቢከብር፣ ሌሎቹም ብልቶች ዐብረው ደስ ይላቸዋል።


እንግዲህ በጌታ እስረኛ የሆንሁ እኔ፣ ለተቀበላችሁት ጥሪ የሚገባ ኑሮ ትኖሩ ዘንድ እለምናችኋለሁ።


ይህን ሰላምታ በገዛ እጄ የጻፍሁት እኔ ጳውሎስ ነኝ። እስራቴን አስቡ። ጸጋ ከእናንተ ጋራ ይሁን።


እናንተ ራሳችሁ የተሻለና ለዘወትር የሚኖር ሀብት ያላችሁ መሆናችሁን ስለምታውቁ ለታሰሩት ራራችሁ፤ ንብረታችሁም ሲዘረፍ በደስታ ተቀበላችሁ።


በድንጋይ ተወገሩ፤ በመጋዝ ለሁለት ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተወግተው ሞቱ፤ እየተጐሳቈሉ፣ እየተሰደዱና እየተንገላቱ የበግና የፍየል ቈዳ ለብሰው ዞሩ፤


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ሐሳብ ተስማሙ፤ እርስ በርሳችሁ ተሳሰቡ፤ እንደ ወንድማማቾች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


跟着我们:

广告


广告