Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 13:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሊቀ ካህናቱ ስለ ኀጢአት ስርየት የሚሆነውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ ሥጋ ግን ከሰፈር ውጭ ይቃጠላል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት የእንስሶችን ደም ወደ ቅድስት ያቀርባል፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የአይሁድ የካህናት አለቃ የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኘውን የእንስሳት ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል፤ የእንስሳቱ በድን ግን ከሰፈሩ ውጪ ይቃጠላል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሊቀ ካህ​ናቱ የሚ​ሠ​ዉ​ትን እን​ስሳ ደም ስለ ኀጢ​አት ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ያቀ​ርብ ነበ​ርና፤ ሥጋ​ው​ንም ከሰ​ፈር ውጭ ያቃ​ጥ​ሉት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሊቀ ካህናት ስለ ኃጢአት ወደ ቅድስት የእንስሶችን ደም ያቀርባልና፤ ሥጋቸው ግን ከሰፈሩ ውጭ ይቃጠላል።

参见章节 复制




ዕብራውያን 13:11
13 交叉引用  

ነገር ግን የወይፈኑን ሥጋ፣ ቈዳውንና ፈርሱን ከሰፈር ውጭ አቃጥለው፤ የኀጢአት መሥዋዕት ነው።


ወይፈኑን ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ወስደህ፣ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ከመቅደሱ ውጩ ለዚሁ ተብሎ በተመደበው ስፍራ ታቃጥለዋለህ።


ደማቸው ለማስተስረያነት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የገባው፣ ለኀጢአት መሥዋዕት የቀረቡት ወይፈንና ፍየል ከሰፈር ውጭ ተወስደው ቈዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸው ይቃጠል።


ከዚያም ልብሱን አውልቆ ሌላ ልብስ ይቀይር፤ ዐመዱንም ተሸክሞ ከሰፈር ውጭ በአምልኮው ሥርዐት መሠረት ንጹሕ ወደ ሆነ ስፍራ ይውሰድ።


ነገር ግን ደሙ ማስተስረያ እንዲሆን ወደ መገናኛው ድንኳን ወደ ቅድስት የቀረበው የኀጢአት መሥዋዕት ሁሉ በእሳት ይቃጠል እንጂ አይበላ።


ሥጋውንና ቍርበቱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለው።


ልጆቹም ደሙን አመጡለት፤ እርሱም ጣቱን በደሙ ውስጥ ነክሮ የመሠዊያውን ቀንዶች ቀባ፤ የተረፈውንም ደም በመሠዊያው ግርጌ አፈሰሰው።


ለካህኑ ለአልዓዛርም ስጠው፤ ከሰፈሩ አውጥተውም በፊቱ ይረዷት።


ከዚህ በኋላ ካህኑ ልብሱን በውሃ ማጠብ፣ ሰውነቱንም መታጠብ አለበት፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ ሊመለስ ይችላል፤ ይሁን እንጂ በሥርዐቱ መሠረት እስከ ማታ ድረስ የረከሰ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告