Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕብራውያን 12:26 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜ ድምፁ ያናወጠው ምድርን ነበር፤ አሁን ግን፣ “አንድ ጊዜ እንደ ገና ምድርን ብቻ ሳይሆን፣ ሰማያትንም አናውጣለሁ” ብሎ ቃል ገብቷል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ቃሉ ምድርን አናውጦአል፤ አሁን ግን “ምድርን ብቻ ሳይሆን አንድ ጊዜ ደግሜ ሰማይን ጭምር አናውጣለሁ” በማለት ቃል ገብቶአል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ያን​ጊዜ ቃል ምድ​ርን አና​ወ​ጣት፤ “አሁ​ንም እኔ ምድ​ርን እንደ ገና አንድ ጊዜ አና​ው​ጣ​ታ​ለሁ” ብሎ ተና​ገረ፤ ምድ​ርን ብቻም አይ​ደ​ለም፤ ሰማ​ይ​ንም ጭምር እንጂ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በዚያም ጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጠ፥ አሁን ግን፦ አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።

参见章节 复制




ዕብራውያን 12:26
12 交叉引用  

የሲና ተራራ እግዚአብሔር በእሳት ስለ ወረደበት በጢስ ተሸፍኖ ነበር። ጢሱ ከምድጃ እንደሚወጣ ጢስ ወደ ላይ ተትጐለጐለ፤ ተራራውም በሙሉ በኀይል ተናወጠ።


ስለዚህ በሰራዊት ጌታ በእግዚአብሔር መዓት፣ ቍጣው በሚነድድበት ቀን፣ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ።


እግዚአብሔር ምድርን ለማናወጥ በሚነሣበት ጊዜ፣ ሰዎች ከአስፈሪነቱ ከግርማውም የተነሣ፣ ወደ ዐለት ዋሻ፣ ወደ መሬትም ጕድጓድ ለመሸሸግ ይሮጣሉ።


“እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማያትና አዲስ ምድር በፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፣ የእናንተና የዘራችሁ ስም እንደዚሁ ጸንቶ ይኖራል” ይላል እግዚአብሔር፤


እግዚአብሔር ከጽዮን ጮኾ ይናገራል፤ ከኢየሩሳሌም ያንጐደጕዳል፤ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፤ እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፣ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።


ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤ የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ ቀላዩ ደነፋ፤ ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።


“ለይሁዳ ገዥ ለዘሩባቤል ሰማያትንና ምድርን እንደማናውጥ ንገረው፤


የመንግሥታትን ዙፋን እገለብጣለሁ፤ የባዕዳንን መንግሥታት ኀይል አጠፋለሁ፤ ሠረገሎችንና ሠረገለኞችን እገለብጣለሁ፤ ፈረሶችና ጋላቢዎቻቸውም በገዛ ወንድሞቻቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።


አንድ ጊዜ “ደግሜ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው የማይናወጡት ጸንተው ይኖሩ ዘንድ፣ የሚናወጡት ይኸውም፣ የተፈጠሩት የሚወገዱ መሆናቸውን ነው።


“እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሴይር በወጣህ ጊዜ፣ ከኤዶም ምድርም በተነሣህ ጊዜ፣ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያትም ዝናብ አዘነቡ፤ ደመናዎችም ውሃ አፈሰሱ።


跟着我们:

广告


广告