ሐጌ 1:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ብዙ ዘራችሁ፤ ነገር ግን ያጨዳችሁት ጥቂት ነው። በላችሁ፤ ግን አልጠገባችሁም። ጠጣችሁ፤ ግን አልረካችሁም። ለበሳችሁ፤ ግን አልሞቃችሁም። ደመወዝን ተቀበላችሁ፤ ግን በቀዳዳ ኰረጆ የማስቀመጥ ያህል ነው።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እነሆ ብዙ ዘርታችሁ ጥቂት ሰበሰባችሁ፤ ትበላላችሁ፤ ነገር ግን አትጠግቡም፤ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን አትረኩም፤ ደራርባችሁ ትለብሳላችሁ፤ ነገር ግን አይሞቃችሁም፤ ሠርታችሁ የምታገኙት ደመወዝ ስለማይበረክትላችሁ፥ በቀዳዳ ኪስ ውስጥ የማኖር ያኽል ይሆናል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፣ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፣ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፣ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፣ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፥ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፥ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልረካችሁም፥ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፥ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ያደርገው ዘንድ ደመወዙን ተቀበለ። 参见章节 |