Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዕንባቆም 2:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ሰዎች፣ ለእሳት ማገዶ እንዲሆን እንዲለፉ፣ ሕዝቦችም በከንቱ እንዲደክሙ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖ የለምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ሰዎች የሚሠሩት ለቃጠሎ፥ መንግሥታትም የሚደክሙት ምንም ጥቅም ለሌለው ነገር እንዲሆን የሚያደርግ የሠራዊት አምላክ አይደለምን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነሆ፥ አሕዛብ ስለ እሳት እንዲሠሩ፥ ወገኖችም ስለ ከንቱነት እንዲደክሙ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሆነ አይደለምን?

参见章节 复制




ዕንባቆም 2:13
12 交叉引用  

በዚህ ጊዜ፣ “ከአቤሴሎም ጋራ ካሤሩት መካከል አንዱ አኪጦፌል ነው” ብለው ለዳዊት ነገሩት። ስለዚህ ዳዊት፣ “እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህን የአኪጦፌልን ምክር ወደ ከንቱነት ለውጠው” ብሎ ጸለየ።


“ሰው የጥላ ውልብታ ነው፤ በከንቱም ይታወካል፤ ለማን እንደሚሆን ሳያውቅ ሀብት ንብረት ያከማቻል።


እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣ አንዳችም ጥበብ፣ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።


አሁን ግን እናንተ እሳት አንድዳችሁ፣ የራሳችሁን የሚንቦገቦግ ችቦ የያዛችሁ ሁሉ፣ በሉ በእሳታችሁ ብርሃን ሂዱ፤ ባንቦገቦጋችሁትም የችቦ ብርሃን ተመላለሱ። እንግዲህ ከእጄ የምትቀበሉት ይህ ነው፤ በሥቃይም ትጋደማላችሁ።


ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች።


የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤ የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”


እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ” የኤርምያስ ትንቢት እዚህ ላይ አበቃ።


ኤዶምያስ፣ “ብንደመሰስም እንኳ የፈረሰውን መልሰን እንሠራዋለን” ይል ይሆናል። የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፤ “እነርሱ ይሠሩ ይሆናል፤ እኔ ግን አፈርስባቸዋለሁ፤ ክፉ ምድር፣ እግዚአብሔርም ለዘላለም የተቈጣው ሕዝብ ተብለው ይጠራሉ።


跟着我们:

广告


广告