ዕንባቆም 2:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፤ በምሽጉ ቅጥር ላይ ወጥቼ እቈያለሁ፤ ምን እንደሚለኝ፣ ለክርክሩም የምሰጠውን መልስ ለማወቅ እጠባበቃለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፤ ምን እንደሚለኝና በአቤቱታዬም ምን መልስ እንደምሰጥ ለማየት እጠባበቃለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፣ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 በመጠበቂያዬ ላይ እቆማለሁ፥ በአምባ ላይም እወጣለሁ፥ የሚናገረኝንም፥ ስለ ክርክሬም የምመልሰውን አውቅ ዘንድ እመለከታለሁ። 参见章节 |