Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 50:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንደዚሁም የዮሴፍ ቤተ ሰዎች፣ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተ ሰዎች በሙሉ ዐብረውት ሄዱ። በጌሤም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፣ የበግ፣ የፍየልና የከብት መንጋዎቻቸው ብቻ ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የዮሴፍም ቤተሰቦች ሁሉ፥ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ፥ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተዉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲሁም የዮሴፍ ቤተሰቦች፥ ወንድሞቹና ሌሎችም የአባቱ ቤተሰቦች ሁሉ ከዮሴፍ ጋር ሄዱ፤ በጌሴም የቀሩት ሕፃናት ልጆቻቸው፥ በጎቻቸው፥ ፍየሎቻቸውና ከብቶቻቸው ብቻ ነበሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የዮ​ሴ​ፍም ቤተ ሰቦች ሁሉ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹም፥ የአ​ባ​ቱም ቤተ ሰቦች ወጡ፤ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና በጎ​ቻ​ቸ​ውን፥ ከብ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ብቻ በጌ​ሤም ተዉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የዮሴፍም ቤተ ስቦች ሁሉ ወንድሞቹም የአባቱም ቤተሰቦች ወጡ ልጆቻቸውንና በጎቻቸውን ከብቶቻቸውን ብቻ በጌሤም ተው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 50:8
5 交叉引用  

ከዚያም ዮሴፍ አባቱን ለመቅበር ወጣ፤ የፈርዖን ሹማምት በሙሉ፣ የቤተ መንግሥቱ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች እንዲሁም የግብጽ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች ሁሉ ተከተሉት።


እንዲሁም ሠረገሎችና ፈረሰኞች ዐብረውት ወጡ፤ አጀቡም እጅግ ብዙ ነበረ።


እንስሶቻችን ሁሉ ዐብረው መሄድ አለባቸው። አንድ ሰኰና እንኳ አይቀርም። ከእንስሶቻችን መካከል ለአምላካችን ለእግዚአብሔር አምልኮ የምናቀርባቸው ይኖራሉ፤ ሆኖም እዚያ ከመድረሳችን በፊት እግዚአብሔርን ለማምለክ የምናቀርባቸው እንስሳት የትኞቹ እንደ ሆኑ አስቀድመን ለይተን ማወቅ አንችልም።”


跟着我们:

广告


广告