Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 44:17 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዮሴፍም፣ “ይህንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባሪያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዮሴፍም፥ “ይህንንስ ፈጽሞ አላደርገውም፤ ባርያዬ የሚሆነው ጽዋው የተገኘበት ሰው ብቻ ነው፤ የቀራችሁት በሰላም ወደ አባታችሁ ተመለሱ” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ዮሴፍም “ይህንንስ ከቶ አላደርገውም! ዋንጫው የተገኘበት ሰው ብቻ የእኔ ባሪያ መሆን አለበት፤ ሌሎቻችሁ በሰላም ወደ አባታችሁ መመለስ ትችላላችሁ!” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ይህን አደ​ርግ ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ጽዋው የተ​ገ​ኘ​በት ሰው እርሱ አገ​ል​ጋይ ይሁ​ነኝ እንጂ፤ እና​ንተ ግን ወደ አባ​ታ​ችሁ በደ​ኅና ሂዱ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 44:17
10 交叉引用  

እንዲህስ አይሁን፤ ጻድቁን ከኀጢአተኛው ጋራ እንዴት ትገድለዋለህ? ይህን የመሰለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ፤ የምድር ሁሉ ዳኛ በቅን አይፈርድምን?”


አንተን እንዳልጐዳንህ፣ ነገር ግን በጎነትን እንዳሳየንህና በሰላም እንደ ሸኘንህ ሁሉ፣ አንተም ክፉ እንዳታደርግብን በመካከላችን ውል ይደረግ፤ አንተን እንደሆን መቼም እግዚአብሔር ባርኮሃል።”


በሦስተኛውም ቀን ዮሴፍ እንዲህ አላቸው፤ “እኔ እግዚአብሔርን ስለምፈራ እንዲህ በማድረግ ሕይወታችሁን አትርፉ።


እርሱም “መልካም ነው፤ እንዳላችሁት ይሁን፤ ጽዋው የተገኘበት ሰው ባሪያዬ ይሆናል፤ የቀራችሁት ግን ከበደሉ ነጻ ትሆናላችሁ” አላቸው።


ይሁዳም፣ “ከእንግዲህ ለጌታችን ምን ማለት እንችላለን? ምንስ እንመልሳለን? እንዲህ ካለው በደል ንጹሕ መሆናችንን ማስረዳትስ እንዴት ይቻለናል? እግዚአብሔር የእኛን የአገልጋዮችህን በደል ገልጧል፤ ከእንግዲህ ጽዋው የተገኘበት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ባሮችህ ነን” አለ።


ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖንን ያህል የተከበርህ ስለ ሆንህ፣ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።


የእስራኤል አምላክ ተናገረ፤ የእስራኤልም ዐለት እንዲህ አለኝ፤ ‘ሰዎችን በጽድቅ የሚገዛ፣ በፈሪሀ እግዚአብሔርም የሚያስተዳድር፣


አንተም እንዲህ አልህ፤ “ለይቼ በወሰንኋት ሰዓት፣ በቅን የምፈርድ እኔ ነኝ።


በደለኛውን ማጽደቅ ሆነ፣ ጻድቁን በደለኛ ማድረግ፣ ሁለቱም በእግዚአብሔር ዘንድ አስጸያፊ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告