Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 43:15 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሰዎቹም እጅ መንሻውን፣ የብሩን ዕጥፍ እንዲሁም ብንያምን ይዘው ተነሡ፤ ወደ ግብጽም በፍጥነት ወረዱ፤ ዮሴፍም ፊት ቀረቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእስራኤልም ልጆች እጅ መንሻውን፥ የብሩን ዕጥፍ እንዲሁም ብንያምን ይዘው ተነሡ፤ ወደ ግብጽም በፍጥነት ወረዱ፤ ዮሴፍም ፊት ቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ወንድማማቾቹ ገጸ በረከቱንና እጥፍ ገንዘብ ይዘው ከብንያም ጋር ወደ ግብጽ ለመሄድ ጒዞ ጀመሩ፤ እዚያም በደረሱ ጊዜ ወደ ዮሴፍ ፊት ቀረቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሰዎ​ቹም በእ​ጃ​ቸው ያችን እጅ መን​ሻና ብራ​ቸ​ውን በእ​ጥፍ፥ ብን​ያ​ም​ንም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ወሰዱ፤ ተነ​ሥ​ተ​ውም ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዮ​ሴ​ፍም ፊት ቆሙ፤ ሰገ​ዱ​ለ​ትም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ሰዎቹም በእጅቸው ያችን እጅ መንሻና አጠፌታውን ብር ብንያምንም ወሰዱ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በዮሴፍም ፊት ቆሙ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 43:15
6 交叉引用  

እህሉንም ሲዘረግፉ በየስልቾቻቸው ውስጥ ብራቸው እንደ ተቋጠረ ተገኘ፤ የእያንዳንዳቸውን የተቋጠረ ብር ሲያዩም፣ እነርሱም ሆኑ አባታቸው ደነገጡ።


ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።


ነገር ግን ለዐዳር በሰፈርንበት ቦታ የየስልቾቻችንን አፍ ስንከፍት፣ እያንዳንዳችን በስልቾቻችን አፍ ላይ፣ ብራችንን ሙሉውን አገኘነው። ገንዘቡንም ይኸው መልሰን ይዘን መጥተናል።


ምሳ በዚያ እንደሚበሉ ተነግሯቸው ስለ ነበር፣ ዮሴፍ በቀትር ከመግባቱ በፊት እጅ መንሻዎቻቸውን ለማበርከት ተዘጋጁ።


ጦረኛው ኤፍሬማዊ ዝክሪም የንጉሡን ልጅ መዕሤያን፣ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ የሆነውን ዓዝሪቃምንና ለንጉሡ በማዕርግ ሁለተኛ ሰው የሆነውን ሕልቃናን ገደለ።


ብዙ ሰዎች በገዥ ዘንድ ሞገስ ለማግኘት ያሸረግዳሉ፤ ስጦታን ከሚሰጥ ሰው ጋራ ሁሉም ወዳጅ ነው።


跟着我们:

广告


广告