Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 39:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በቀር፣ ማንኛውንም ጕዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ስለዚህ ጲጥፋራ ባለው ሁሉ ላይ ሥልጣን ሰጠው፤ የቀረበለትንም ከመመገብ በስተቀር፥ ማናቸውንም ጉዳይ በዮሴፍ ላይ ጥሎ ነበር። ዮሴፍ ጥሩ ቁመና ያለውና መልከ መልካም ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ስለዚህ ጶጢፋር ያለውን ንብረት ሁሉ በዮሴፍ ቊጥጥር ሥር አደረገ፤ ጶጢፋር ከሚመገበው ምግብ በስተቀር የሚያውቀው ምንም ነገር አልነበረም። ዮሴፍ ቁመናው የተስተካከለ መልከ መልካም ሰው ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ያለ​ው​ንም ሁሉ ለዮ​ሴፍ በእጁ አስ​ረ​ከ​በው፤ ከሚ​በ​ላ​ውም እን​ጀራ በቀር ምንም የሚ​ያ​ው​ቀው አል​ነ​በ​ረም። ዮሴ​ፍም መልኩ ያማረ፥ ፊቱም እጅግ የተ​ዋበ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴርም ፊቱ መልከ መልካምን ውብ ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 39:6
12 交叉引用  

ልያ ዐይነ ልም ስትሆን ራሔል ግን ቁመናዋ ያማረ መልኳም የተዋበ ነበር።


እግዚአብሔር ከዮሴፍ ጋራ ሆኖ ሥራውን ሁሉ ያሳካለት ስለ ነበር፣ የወህኒ ቤት አዛዡ በዮሴፍ ኀላፊነት ሥር ስላለው ስለ ማንኛውም ጕዳይ ሐሳብ አይገባውም ነበር።


ዮሴፍ በርሱ ዘንድ ሞገስ አገኘ፤ የቅርብ አገልጋዩም ሆነ። ጲጥፋራ በቤቱ ላይ ሾመው፤ ያለውንም ሀብት ሁሉ በኀላፊነት ሰጠው።


እርሱ ግን ፈቃደኛ አልሆነም፤ እንዲህም አላት፤ “ጌታዬ ያለውን ሁሉ በኀላፊነት ስለ ሰጠኝ፣ በቤቱ ውስጥ ስላለው ሁሉ ምንም የሚያውቀው ነገር የለም።


ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከርሱ ጋራ ለሚበሉት ግብጻውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብጻውያን ከዕብራውያን ጋራ ዐብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።


ባሏ ሙሉ በሙሉ ይተማመንባታል፤ የሚጐድልበትም ነገር የለም።


“በትንሽ ነገር ታማኝ የሆነ በትልቁም ይታመናል፤ በትንሽ ነገር ያልታመነ በትልቁም አይታመንም።


“ጌታውም፣ ‘አንተ ታማኝ ባሪያ፣ መልካም አድርገሃል፤ በትንሽ ነገር ታማኝ ሆነህ ስለ ተገኘህ፣ በዐሥር ከተሞች ላይ ሥልጣን ተሰጥቶሃል’ አለው።


“በዚህ ጊዜ ሙሴ ተወለደ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስን ያገኘ ውብ ሕፃን ነበር። በአባቱም ቤት ሦስት ወር በእንክብካቤ አደገ።


ስለዚህ ልኮ አስመጣው፤ እርሱም ደም ግባት ያለው፣ ዐይኑ የሚያምርና መልከ መልካም ነበረ። እግዚአብሔርም፣ “የመረጥሁት ይህ ነውና ተነሥተህ ቀባው” አለው።


ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን ትኵር ብሎ ሲያየው፣ ደም ግባት ያለው፣ መልከ መልካምና አንድ ፍሬ ልጅ ነበር፤ ስለዚህ ናቀው።


跟着我们:

广告


广告