Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 36:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ዔሳው ሚስቶቹን፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፣ ቤተ ሰቦቹን በሙሉ እንደዚሁም የቀንድ ከብቶቹንና ሌሎቹንም እንስሳት ሁሉ በከነዓን ምድር ያፈራውን ሀብት እንዳለ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ዔሳውም ሚስቶቹን፥ ወንዶች ልጆቹንና ሴቶች ልጆቹን፥ ቤተሰቡንም ሁሉ፥ እንስሶቹንም ሁሉ፥ በከነዓንም ሀገር ያገኘውን ንብረቱን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ከዚህ በኋላ ዔሳው ሚስቶቹን ወንዶችና ሴቶች ልጆቹን፥ በቤቱ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ መንጋዎቹንና ሌሎቹንም ከብቶች ሁሉ፥ በከነዓን ሳለ ያፈራውን ንብረት ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ራቅ ወዳለ ቦታ ሄደ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ዔሳ​ውም ሚስ​ቶ​ቹን፥ ወን​ዶች ልጆ​ቹ​ንና ሴቶች ልጆ​ቹን፥ ቤተ ሰቡ​ንም ሁሉ፥ እን​ስ​ሶ​ቹ​ንም ሁሉ፥ በከ​ነ​ዓ​ንም ሀገር ያገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ይዞ ከወ​ን​ድሙ ከያ​ዕ​ቆብ ፊት ከከ​ነ​ዓን ሀገር ሄደ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ዔሳውም ሚስቶቹን ወንዶች ልጅቹንና ሴቶች ልጆቹን ቤተሰቡንም ሁሉ ከብቱንም ሁሉ እንስሶቹንም ሁሉ በከንዓንም አገር ያገኘውን ሁሉ ይዞ ከወንድሙ ከያዕቆብ ፊት ወደ ሌላ አገር ሄደ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 36:6
10 交叉引用  

አብራምም ሚስቱን ሦራንና የወንድሙን ልጅ ሎጥን አስከትሎ በካራን ሳሉ ያፈሩትን ሀብትና የነበራቸውን አገልጋዮች ይዘው በመጓዝ ከነዓን ምድር ገቡ።


ሎጥ የዮርዳኖስን ረባዳ ሜዳ በሙሉ መርጦ ወደ ምሥራቅ አመራ፤ ሁለቱ ሰዎች በዚሁ ተለያዩ።


ሆኖም ሁለቱ አንድ ላይ ሲኖሩ ስፍራው አልበቃቸውም፤ ንብረታቸው እጅግ ብዙ ስለ ነበር፣ ዐብረው መኖር አልቻሉም።


ይህችን አሁን በእንግድነት የምትኖርባትን የከነዓንን ምድር በሙሉ ለአንተና ከአንተም በኋላ ለዘርህ ለዘላለም ርስት አድርጌ እሰጣቸዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ።”


እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።


እግዚአብሔር ለአብርሃም ሰጥቶ የነበረውን አንተም በስደት የምትኖርበትን ይህችን ምድር ርስት አድርጎ ያወርስህ ዘንድ፣ ለአብርሃም የሰጠውን በረከት ለአንተና ለዘርህ ይስጥ።”


ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤


እንደዚሁም ኦሆሊባማ የዑስን፣ የዕላምንና ቆሬን ወለደችለት፤ እነዚህ ዔሳው በከነዓን አገር የወለዳቸው ልጆች ናቸው።


“ ‘ያዋን፣ ቶቤልና ሜሼኽ ከአንቺ ጋራ ይነግዱ ነበር፤ ባሪያዎችንና የናስ ዕቃዎችን በሸቀጥሽ ይለውጡ ነበር።


ቀረፋ፣ ቅመም፣ ከርቤ፣ ቅባት፣ ዕጣን፣ የወይን ጠጅ፣ የወይራ ዘይት፣ የተሰለቀ ዱቄት፣ ስንዴ፣ ከብቶች፣ በጎች፣ ፈረሶች፣ ሠረገሎች፣ እንዲሁም ባሮችና የሰዎች ነፍሶች ነው።


跟着我们:

广告


广告