ዘፍጥረት 36:43 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም43 መግዲኤል እና ዒራም። እነዚህ በያዙት ምድር እንደየይዞታቸው የኤዶም ዘሮች የነገድ አለቆች ነበሩ። ይህም ዔሳው፣ የኤዶማውያን አባት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)43 ማግዲኤል አለቃ፥ ዒራም አለቃ፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ዔሳው ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም43 ማግዲኤልና ዒራም። በየመኖሪያ ስፍራቸው ስም የሚጠሩት የኤዶም አለቆች እነዚህ ናቸው። ይህም ዔሳው የኤዶማውያን አባት ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)43 መግዴኤል መስፍን፥ ኤራም መስፍን፤ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም መሳፍንት ናቸው። የኤዶማውያንም አባት ይህ ዔሳው ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)43 መግዲኤል አለቃ ዒራም አለቃ፥ እነዚህ በግዛታቸው ምድር በየመኖሪያቸው የኤዶም አለቆች ናቸው። የኤዶማውያን አባት ይህ ዔሳው ነው። 参见章节 |