Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 36:31 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 በእስራኤል ምንም ንጉሥ ከመንገሡ በፊት፣ በኤዶም ምድር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው፦

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 በእስራኤል ንጉሥ መንገሥ ከመጀመሩ በፊት በኤዶም ምድር የነገሡት ነገሥታት የሚከተሉት ናቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመ​ን​ገሡ በፊት በኤ​ዶም ሀገር የነ​ገሡ ነገ​ሥ​ታት እነ​ዚህ ናቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 በእስራኤል ልጆች ላይ ንጉሥ ከመኖሩ በፊት በኤዶም አገር የነገሡ ነገሥታት እነዚህ ናቸው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 36:31
11 交叉引用  

እኔ እባርካታለሁ ከርሷም ወንድ ልጅ እሰጥሃለሁ፤ የብዙም ሕዝቦች እናት ትሆን ዘንድ እባርካታለሁ፤ የሕዝቦችም ነገሥታት ከርሷ ይወጣሉ።”


ዘርህን እጅግ አበዛለሁ፤ ብዙ ሕዝብም አደርግሃለሁ፤ ነገሥታትም ከአንተ ይወጣሉ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አላት፤ “ሁለት ወገኖች በማሕፀንሽ አሉ፤ ሁለትም ሕዝቦች ከውስጥሽ ተለያይተው ይወጣሉ፤ አንደኛው ከሌላው ይበረታል፤ ታላቁም ለታናሹ ይገዛል” አላት።


ደግሞም እግዚአብሔር ያዕቆብን እንዲህ አለው፤ “እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝ፤ ብዛ ተባዛ፤ ሕዝብና የሕዝቦች ማኅበር ከአንተ ይወጣሉ፤ ነገሥታትም ከአብራክህ ይከፈላሉ።


ዲሶን፣ ኤጽርና ዲሳን። እነዚህ በሴይር ምድር እንደየነገዳቸው የሖሪውያን የነገድ አለቆች ነበሩ።


ሙሴ ከቃዴስ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ሲል መልእክተኞች ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል የሚለው ይህ ነው፤ የደረሰብን መከራ ሁሉ ምን እንደ ሆነ አንተም ታውቃለህ።


ብፁዕ ነህ፤ አንተ እስራኤል ሆይ፤ እግዚአብሔር ያዳነው ሕዝብ፣ እንደ አንተ ያለ ማን አለ? እርሱ ጋሻህና ረዳትህ፣ የክብርህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህ በፍርሀት ከፊትህ ያፈገፍጋሉ፤ አንተም የማምለኪያ ኰረብታቸውን መረማመጃ ታደርጋለህ።”


የሕዝቡ አለቆች ከእስራኤል ነገዶች ጋራ ሆነው፣ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣ እርሱ በይሹሩን ላይ ንጉሥ ነበር።


跟着我们:

广告


广告