Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 35:7 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ያዕቆብም በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠርቶ፣ ስሙን ኤል-ቤቴል አለው፤ ምክንያቱም ከወንድሙ ሸሽቶ በሄደ ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ቦታ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በዚያም መሠዊያውን ሠራ፥ የዚያንም ቦታ ስም “ኤልቤቴል” ብሎ ጠራው፥ እርሱ ከወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጦለት ነበርና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ያዕቆብ እዚያ መሠዊያ ሠርቶ “ኤል ቤትኤል” ብሎ ሰየመው፤ ከወንድሙ ፊት ሸሽቶ በሄደበት ጊዜ እግዚአብሔር የተገለጠለት በዚህ ስፍራ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን ሠራ፤ የዚ​ያ​ንም ቦታ ስም ቤቴል ብሎ ጠራው፤ እርሱ ከወ​ን​ድሙ ከዔ​ሳው ፊት በሸ​ሸ​በት ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚያ ተገ​ል​ጦ​ለት ነበ​ርና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በዚያንም ቦታ ስም ኤልቤቴል ብሎ ጠራው እርሱ ለወንድሙ ፊት በሸሸበት ጊዜ እግዚአብሔር በዚያ ተገልጣለት ነበርና

参见章节 复制




ዘፍጥረት 35:7
16 交叉引用  

እግዚአብሔርም ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ።


ከዚያም ተነሥቶ ከቤቴል በስተምሥራቅ ወዳሉት ተራሮች ሄደ፤ ቤቴልን በምዕራብ፣ ጋይን በምሥራቅ አድርጎ ድንኳን ተከለ፣ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ጸለየ።


ያዕቆብ ከቤርሳቤህ ተነሥቶ ወደ ካራን ሄደ።


እግዚአብሔርም ከጫፉ ላይ ቆሞ እንዲህ አለ፤ “የአባትህ የአብርሃም አምላክ፣ የይሥሐቅ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ የተኛህበትን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ።


እርሱም በፍርሀት፣ “ይህ ስፍራ እንዴት የሚያስፈራ ነው! ይህስ ሌላ ሳይሆን የእግዚአብሔር ቤት መሆን አለበት፤ የሰማይ ደጅ ነው” አለ።


ያን ቦታ ቤቴል ብሎ ሰየመው፤ ቀደም ሲል ግን የከተማዪቱ ስም ሎዛ ነበር።


ይህ ሐውልት አድርጌ ያቆምሁት ድንጋይ፣ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፤ ከምትሰጠኝም ሀብት ሁሉ፣ ከዐሥር እጅ አንዱን ለአንተ እሰጣለሁ።”


ያዕቆብም ጕዞውን ቀጠለ፤ የምሥራቅም ሰዎች ወደሚኖሩበት ምድር ደረሰ።


የድንጋይ ሐውልት በማቆም ዘይት ቀብተህ የተሳልህባት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ፤ አሁንም ይህን አገር ፈጥነህ ልቀቅና ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመልሰህ ሂድ’ አለኝ።”


እግዚአብሔር ያዕቆብን፣ “ተነሥና ወደ ቤቴል ውጣ፤ እዚያም ተቀመጥ፤ ከወንድምህ ከዔሳው ሸሽተህ በሄድህ ጊዜ ለተገለጠልህ አምላክ በዚያ መሠዊያ ሥራ” አለው።


ያዕቆብም፣ እግዚአብሔር ከርሱ ጋራ የተነጋገረበትን ስፍራ ቤቴል ብሎ ጠራው።


ተነሥተን ወደ ቤቴል እንውጣ፤ እዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ፣ በሄድሁበትም ስፍራ ሁሉ ላልተለየኝ አምላክ መሠዊያ እሠራለሁ።”


ሙሴም መሠዊያውን ሠርቶ፣ “እግዚአብሔር ዐርማዬ ነው” ብሎ ሰየመው።


“የከተማዪቱም ዙሪያ ዐሥራ ስምንት ሺሕ ክንድ ይሆናል፤ “የከተማዪቱ ስም፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ‘እግዚአብሔር በዚያ አለ’ ” ይሆናል።


ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “እግዚአብሔር ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።


跟着我们:

广告


广告